/ Categories: CASSATION, Cassation

ልማት ፋና የደን ማሕበር እና የአቶ አበበ ወልደየስ ሚስትና ወራሾች የሰ/መ/ቁ 200816

ጉዳዩ የተጠሪዎች አባት የተከሉትን ባሕር ዛፍ ከሕግ ውጪ ቆርጦ ወስዶል የተባለወን አመልካች የባህር ዛፉን   ግምት ለማስከፈል የቀረበ የንብረት ክርክርን የሚመለከት ሆኖ አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጀመረው ክርክር የአሁን ተጠሪዎች ከሣሽ አመልካች ደግሞ ተከሣሽ ነበሩ፡፡

ተጠሪዎች ሰኔ 6ቀን 2008ዓ/ም በተፃፈ ክሳቸው በደሴ ከተማ ቧንቧ ውሐ ክፍለ ከተማ ሟች አባታቸው በሊዝ የመሬት ስሪት ስርዓት ይዘው ለከተማ ግብርና ከሚጠቀሙበት 1035 ካሬ ሜትር ስፋት ካለው ይዞታቸው አዋሣኝ የሆነው መሬት ላይ ወደ ደሴ ከተማ የሚገባውን ናዳ ለመከላከል  በአካባቢው ማሕበረሰብ ተሣትፎ ባሕር ዛፍ እንዲተከልበት ከደሴ ከተማ አስተዳደር ከተወሰነ በኋላ ማህበረሰቡ ለመትክል ፈቃደኛ ባመለመሆኑ የተጠሪዎች አውራሽ እንዲተክሉበት ተፈቅዶላቸው ብቻቸውን ተክለው ያሣደጉትንና በማህበራዊ ፍርድ ቤትም የተረጋጠላቸውን ባሕር ዛፍ አመልካች ምንም መብት ሣይኖረው 500 አውራጅ፣ 800 ማገር 350 ቋሚ  3000 ጠርዝ በአጠቃለይ ግምቱ 94,000.00 የሚያወጣውን ባሕር ዛፍ ሰኔ 1ቀን 2001ዓ/ም ቆርጦ የተጠቀመበት መሆኑን በመዘርዘር ግምቱን ከልዩ ልዩ ወጪ ጋር እንዲከፍላቸው ጠይቀዋል፡፡…………….

Print
10710

Documents to download

  • 200816(.pdf, 843.32 KB) - 811 download(s)