Friday, July 15, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation ሐጂ ይማም መሀመድ እና አቶ በላቸው /አብዱልሰመድ/ አደም የሰበር መ/ቁ/211987 ጉዳዩ የዋሰትና ዉል የሚመለከት ነዉ፡፡የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ ክርክሩ የተጀመረው በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ በቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን በአሁኑ ተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ ተጠሪ ዋስ ጠርቶኝ ብር 278,000 እቁብ ገንዘብ ወስዶ ብር 153,000 ሳይከፍል በማቋረጡ በገባሁት የዋስትና ግዴታ መሰረት ተጠሪ ያልከፈለውን ገንዘብ የከፈልኩኝ ስለሆነ ተጠሪ ዋናውን ገንዘብ ብር 153,000 ፣የ6ዓመት ከ7 ወር ህጋዊ ወለድ ብር 92,259 እና ኪሳራ ብር 164,583 በድምሩ ብር 409,842 እንዲከፈለኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…… Print 12552 Documents to download 211987(.pdf, 876.79 KB) - 1307 download(s)