Friday, December 31, 2021 / Categories: CASSATION, Judgement, Cassation ሕዳሴ ቴሌኮም አ/ማ እና እነ አቶ ገዛኸኝ ለማ የሰ/መ/ቁ፡200929 የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ከሳሽ፣ ተጠሪዎች ተከሳሾች ሆነው ተከራክረዋል፡፡ አመልካች ያቀረበው ክስ 1ኛ ተጠሪ የአመልካች የሽያጭ ሠራተኛ ሆነው ሲሰሩ በውስጥ ኦዲት በሚደረግበት ጊዜ ብር 204,250.00 በጉድለት ስለተገኘ ገንዘቡን እንዲከፍሉ፤ 2ኛ ተጠሪም የ1ኛ ተጠሪ ዋስና ተያዥ በመሆናቸው እስከ 100,000.00 በአንድነትና ነጠላ ኃላፊነት እንዲከፍሉ የሚል ነው፡፡ 1ኛ ተጠሪ የሠጡት መልስ ገቢና ወጪውን ያልለየ፣ ከመቼ እስከመቼ የተደረገ ኦዲት ስለመሆኑ ግልጽ አይደለም፡፡ በውጭ ኦዲተር ኦዲት ይደረግልኝ ብለዋል፡፡ 2ኛ ተጠሪ በበኩላቸው ጉድለት የለም፣ ዋስ የሆንኩት 1ኛ ተጠሪ የመስመር ሠራተኛ እያለ ነው፤ ልጠየቅ አይገባም በማለት ተከራክረዋል፡፡…………. Previous Article አይካ አዲስ ጨርቃ ጨርቅ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና አቶ ኢብራሒም አይዶግዱ የሰ/መ/ቁ፡-200687 Next Article መ/ር ሲራጅ መሀመድ እና የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ሰ/መ/ቁ፡-200948 Print 12140 Documents to download 200929(.pdf, 745.68 KB) - 870 download(s)