/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

መሀመድ አባ ቡልጉ እና የጌምቤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የሰ.መ.ቁ 198400

ጉዳዩ የይዞታ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጅማ ዞን ጎማ ወረዳ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በሥር ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች ከሳሽ፤ የአሁን ተጠሪ ተከሳሽ፤ በዚህ የሰበር ክርክር የሌለው የጌምቤ ከተማ መምሕራን ማህበር እነ አቶ ደሳለኝ አበበ / 14 ሰዎች ደግሞ ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ያቀረበው ክስ ይዘት በአጭሩ፡- አመልካች በሕጋዊ መንገድ የያዝኩት አንድ ፈጫሳ የቡና ችግኝ እና አንድ ፈጫሳ ባህር ዛፍ በ 2004 ዓ.ም ተክለው ጸድቆ የነበረ መሆኑን፤ ተጠሪ  ምንም ካሳ ሳይሰጣቸው ከአመልካች ወስዶ ለሰዎች ሲሰጥ የቀረውን አንድ ፈጫሳ በጌምቤ ከተማ ከሶ በር አካባቢ ተብሎ በሚጠራው አዋሳኙ በክሱ ላይ በተገለጸው ይዞታ ውስጥ በቀን 23/09/2011 ዓ.ም በመግባት አጠቃላይ ግምቱ ብር 3830 የሚያወጣ አራት ደጃፍ 3*4 የሆነ 10 ቅጠል ቆርቆሮ ቤት፤ መሪ እንጨት እና ማገር እንዲሁም ከንች ያፈረሰባቸው መሆኑን በመግለጽ አፍርሶ የወሰደውን የንብረት ግምት ብር 3830 / ሶስት ሺሕ ስምንት መቶ ሠላሳ ብር / እንዲከፍላቸው እና በይዞታቸው ላይ የፈጠረው ሁከት እንዲወገድ ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡………..

Previous Article አቶ ተስፋዬ ኪዳኔ እና አቶ ወርቁ ዋበሎ የሰ/መ/ቁጥር 198071
Next Article የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እና አበባየሁ ተዘራ የሰ.መ.ቁ 198703
Print
15179

Documents to download

  • 198400(.pdf, 831.77 KB) - 1307 download(s)