Friday, May 23, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation መርከብ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበር እና አቶ የሽዋስ ገደፍ የሰ.መ.ቁ. 256239 የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን ተጠሪ በሥር ወረዳ ፍ/ቤት ጽፈዉ ባቀረቡት የክስ አቤቱታ፡ ተጠሪ የአመልካች የዱቄት መኖ ማቀናባበሪያ ፋበሪካ ሥራ አስኪያጅ በመሆን በሥራ መሪነት ሳገለግል ቆይቼ ተጠሪ በሰጠዉ ጥቆማ በወንጀል ተጠርጥሬ ከአንድ ታስሬ ነጻ ተልቅቄ ወደ ሥራዬ የተመለስኩኝ ቢሆንም ያለጥፋቴ የታሰርኩኝ በመሆኑ ያለተከፈለኝ ደመወዝ እና ደመወዝ ጭማሪ ከአመት እረፍት ጋር ታስቦ እንዲከለኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡ የአሁን አመልካች በዚህ ላይ ባቀረበዉ መልስ አመልካች የቆሎ ግዥ እንደፈጸመ ተደርጎ በፎርጅት እትመት ሂሳብ ተሰርቶ 1.2 ሚሊዮን ብር በተጭበረበረ መንገድ መዘረፉን በኦዲተሮች በመረጋገጡ ለሚመለከተዉ አካል ጥቆማ መደረጉ ተገቢ ነዉ፤ አመልካች በዚህ መልክ ንብረቱ እንደተጭበረበረ ለፖሊስ ከማሳወቅ በቀር ተጠሪ አጭበርብሯል በማለት የሰጠዉ ጥቆማ የለም፤ ተጠሪ የሥራ መሪ በመሆናቸዉ አመልካች ወደ ሥራ ሊመልሳቸዉ ግዴታ ባይኖርበትም ወደ ሥራ መልሶታል፣ ተጠሪ ላልሰራዉ ሥራ የሚከለፈዉ ደመወዝ ሊኖር አይችልም፤ ተጠሪ ለታሰረዉ ጊዜ ደመወዝ እንዲከፈለዉ የሚደነግግ ሕግ የለም፣ተጠሪ የሥራ መሪ በመሆኑ በፍትሕ ብሔር ሕጉም ሆነ በሥራ ዉሉ መሰረት ላልሰራዉ ሥራ ክፍያ የሚከፈልበት አግባብ የለም፤ የሰዉ ሃይል አደረጃጀት መመሪያ ቁጥር 54/2010 ይህን የሚፈቀድ አይደለም፣ በመሆኑም አመልካች በዚህ ጉዳይ የወንጀልም ሆነ የፍትሕ ብሔር ተጠያቂነት የለበትም ተከራክሯል፡፡መልካም ንባብ …. Print 4635 Documents to download 256239(.pdf, 872.92 KB) - 611 download(s)