Friday, July 15, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation መ/ር ሙሴ አሳየኸኝ የሰበር እና የአ/አ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ መ/ቁ/215321 ጉዳዩ በአስተዳደር አካል የወጣ መመሪያ አግባብነት በፌደራል አስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2013 መሠረት እንዲከለስ የቀረበ አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡ ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረበዉ አቤቱታ ተጠሪ ነሐሴ ወር 2012 ዓ.ም ያወጣው የትምህርት አመራሮች ድልድል መመሪያ ህግን ባልተከተለ መልኩ ስለወጣ መመሪያው ተፈፃሚ እንዳይሆን እና እንዲከለስ የሚል ነዉ፡፡የአቤቱታ ይዘትም አመልካች የአለም ብርሃን የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ-መምህር በመሆን ታህሳስ 12 ቀን 2012 ዓ.ም በፌደራል ደረጃ በወጣው የመምህራን እና ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘር የስራ መደብ የድልድል አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 2/2012 መሰረት አድርጎ ጄ.ጂ.ኤ ጥናት አንቀጽ 9 መሰረት ያለውድድር ከነበረበት ርዕሰ መምህር ኬሪየር በደረጃ 18 ተመድቦ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡መልካም ንባብ….. Print 10656 Documents to download 215321(.pdf, 868.81 KB) - 907 download(s)