/ Categories: CASSATION, 2013, Cassation

ማልድ የትምህርት ድጋፍ ሰጪ ኃ/የተ/የግ/ማህበርበ እናወ/ሪት ብሔር ዮናስ የሰ/መ/ቁ. 218123

ጉዳዩ የተጀመረውም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ ባቀረበችው ክስ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ከመስከረም 04 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ በወር ብር 27,000.00 እየተከፈለኝ በመምህርነት፣ በረዳት አስተዳዳሪነት በልዩ ፍላጎት ዲፓርትመነት የአስተዳደርና ትምህርት ድጋፍ ሰጪ ኃላፊ የስራ መደብ በመሪነት፣ እንዲሁም ሰላሳ በመቶ የሚሆነውን አስተዳደራዊ ስራ እየሰራሁ ያለበቂ ምክንያት የስራ ውሌን ያቋረጠ በመሆኑ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው ተብሎ አመልካች ልዩ ልዩ ክፍያዎች እንዲከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት የጠየቁትን ዳኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡ አመልካች በበኩሉ ተጠሪ የልዩ ፍላጎት ዲፓርትመንት የአስተዳደርና ትምህርት ድጋፍ ሰጪ ኃላፊ የስራ መደብ በመሪነት እንዲሁም ሰላሳ በመቶ የሚሆነውን አስተዳደራዊ ስራ ሲሰሩ የቆዩ የስራ መሪ በመሆናቸዉ የስራ ክርክር ችሎት ጉዳዩን አይቶ የመወሰን የስረ ነገር ስልጣን የለውም የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቧል፡፡መልካም ንባብ…….

Print
14212

Documents to download

  • 218123(.pdf, 826.52 KB) - 1016 download(s)