/ Categories: CASSATION, Judgement, Cassation

ማክሼቭ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና ወጋገን ባንክ አክሲዮን ማህበር የሰ/መ/ቁ፡-201990

ጉዳዩ የብድር ውል ይፍረስልኝ በሚል የቀረበ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ጉዳዩ በተጀመረበት የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡

አመልካች ታህሳስ 18 ቀን 2012 ዓ.ም በተፃፈ ክስ ከተጠሪ ጋር ሚያዝያ 11 ቀን 2011 ዓ.ም በተደረገ የብድር ውል ስምምነት ብር 2,631,246.08 መበደሩን፣ አከፋፈሉም ውሉ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ በየሶስት ወሩ ሁኖ ወለድና የተለያዩ ወጪዎችን ጨምሮ ብር 349,124.00 መሆኑንና በ8 ጊዜ ክፍያ በ2 ዓመት ውስጥ እስከ ሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም ተከፍሎ እንዲጠናቀቅ መስማማታቸውን ነግር ግን ተጠሪ ክፍያው በ7 ጊዜ እንዲጠናቀቅ ማድረጉን፤ ይህም የሒሳብ መዝገብ አያያዝ ላይ ችግር መፍጠሩን፤ የወለድ መጠኑ ላይም ከፍተኛ ልዩነት በማምጣት የተስተካከለ የኦዲት ሪፖርት እንዳይኖር እክል መፍጠሩን፤ በዚህም ምክንያት አመልካች የ2012 ዓ.ም የግብር ክሊራንስ አግኝቶ የንግድ ፍቃዱን ለማሳደስ አለመቻሉን እና ተጠሪም ይህን ለማስተካከል ፍቃደኛ አለመሆኑን ጠቅሶ የብድር ውሉ እንዲፈርስ ዳኝነት ጠይቋል፡፡…………

Previous Article አቶ ታደሰ ንጉሴ እና አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ሻሸመኔ ቅርንጫፍ የሠ/መ/ቁጥር 201974
Next Article አቶ አዲሱ ዓለሙ እና ወ/ሮ መስከረም ንጉሴ የሰ/መ/ቁ፡- 202486
Print
13720

Documents to download

  • 201990(.pdf, 732.4 KB) - 1165 download(s)