Thursday, May 29, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation ምኞት ካሣ ብሩ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የሠ/መ/ቁጥር 270511 አመልካች ለዚህ ችሎት በቀን 06/01/2017 ዓ.ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ በጠበቃዋ አማካኝነት ያቀረበችዉ ከላይ በተጠቀሰው መሰረት የተሰጠው ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት ሲሆን ይዘቱም በአጭሩ - አመልካች በእርግዝና ምክንያት የጤና መታወክ ስለገጠመኝ የሐክም የቅርብ ክትትል እንደሚያስፈልገኝ በመረጋገጡ ለአመልካችም ሆነ ለምወልደዉ ሕጻን ድህንነት በዋስትና ተለቅቄ እንዲከራከር ያቀረብኩትን ጥያቄ የሥር ፍርድ ቤቶች አለመቀበላቸዉ ኢትዮጵያ የተቀበለችዉን ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶች ሰነዶች የሴቶችና የሕጻናትን መብቶች ለማስከበር የወጣዉን ስምምነት አንቀጽ 12/2፣18/2 እና 24(2/መ)ን እና በአፍሪካ የሕጻናት መብቶች ቻርተር አንቀጽ 20(2/ሀ) ስር የተደነገገዉን የሚቃረን ነዉ፡፡በአመልካች ተፈጸመ የተባለዉ የወንጀል ድርጊት ለወደፊት ጥፋተኛ ስትሆን በወንጀል ሕግ አንቀጽ 61/1 መሰረት በአንድ አንቀጽ ስር የሚጠቃለል ሆኖ እያለ የስር ፍርድ ቤቶች አመልካች ለወደፊት የማትቀጣበትን ድንጋጌ ለዋስትና ክልከላ መሠረት በማድረግ የዋስትና መብቷ ሊጠበቅ አይገባም በማለት የሰጡት ዉሳኔ በሰ/መ/ቁጥር 134549 ላይ የተሰጠዉን የሕግ ትርጉም የሚቃረን ነዉ፡፡እንዲሁም አመልካች እንድከላከል ብይን የተሰጠው ከ3 ዓመት በላይ እና ከ10 ዓመት በታች ጽኑ እሥራት በሚያስቀጡ ተደራራቢ ወንጀሎች በመሆኑ የቅጣቱ ድምር ከ10 ዓመት በላይ መሆኑ የዋስትና መብት እንደማያስከለክል እንደገና በተሻሻለው የፀረ ሙስና ልዩ ሥነ ሥርዓትና ማስረጃ አዋጅ ቁጥር 882/007 አንቀጽ 3(1) ተደንግጎ እያለ ይህንን በሚቃረን መልኩ የስር ፍርድ ቤቶች የአመልካችን የዋስትና መብት በመንፈግ የሰጡት ዉሳኔ ስለሆነ ታርሞ የአመልካች የዋስትና መብት ተጠብቆ ይወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል፡፡መልካም ንባብ…. Print 3645 Documents to download 270511(.pdf, 1.05 MB) - 514 download(s)