Monday, June 6, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation ራህዋ አማረ አስመጪ እና የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሞጆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁጥር 204646 ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካች መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ/ም በተፃፈ አቤቱታ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 193949 ጥር 24 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ቅሬታዋን በማቅረቧ ነው፡፡ ቅሬታዋም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካች የምትቃወምባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ሊታይልኝ ይገባል የምትለውን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ አመልካች ያስገባሁትን እቃ ትክክለኛውን ዋጋ አቅርቤ እያለ ተጠሪ ካለ በቂ ምክንያት ህጉን ባልተከተለ መንገድ ውድቅ አድርጎ በ2007 ዓ/ም (2015 እኤአ) የገባ እቃ ከ2 ዓመት በኋላ በ2009 ዓ/ም (2017 እኤአ) በገባ እቃ ጥናት ተደርጎ ቀረጥና ታክስ ተተምኖ ተጨማሪ ቀረጥና ታክስ እንድከፍል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ…….. Print 10713 Documents to download 204646(.pdf, 1.05 MB) - 970 download(s)