Friday, March 13, 2026 / Categories: CASSATION, Cassation ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ: መዝገብ ቁጥር 244308 ጉዳዩ በከተማ ክልል የሚገኝ መሬት ይዞታ መብት ለማስከበር የቀረበ ክስ የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ ነበሩ፡፡ ተጠሪ በ14/11/2013 ዓ/ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ስሙ ፊጋ በሚባል ሰፈር አዋሳኞቹ በክስ የተገለፀውን ግምቱ 2000 ካ.ሜ የሆነ የእርሻ መሬት ከደርግ መንግስት ጀምሮ ተገቢውን የመሬት ግብር በመክፈል ስጠቀምበት የቆየሁትን የእርሻ መሬት ለ11 ዓመት ውጭ ሀገር ቆይቼ ግንቦት 2012 ዓ.ም ወደ ሀገር ቤት ስመለስ ይዞታዬን እንዲያስተዳድሩልኝ ተወካይ አስቀምጬ እያለ አመልካች ምንም ህጋዊ መብት እና የውል ግንኙነት ሳይኖረው ግምቱ ብር 60,000 (ስልሳ ሺህ) የሆነውን ያጠርኩትን አጥር ሰኔ ወር 2011 ዓ.ም በማፍረስ ተወካዬንም ከይዞታው በማባረር ግንብ አጥር በማጠር ቤት ሰርቶ በሕገወጥ መንገድ ይዞታዬን የያዘብኝ በመሆኑ ያለፈቃዴ የገነባውን ቤትና አጥር አፍርሶ በፍ/ሕ/ቁ 1206 መሰረት ይዞታዬን ለቆ ያስረክበኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ Print 3160 Documents to download ሰበር መዝገብ 244308 (1)(.pdf, 551.03 KB) - 681 download(s)