/ Categories: 2013, Cassation

ሲስተር ኮከብ በቀለ ከ እነ ሰላም እስኮዳቮልፕ

እግድ እና የመያዣ ወይም የቅድሚያ መብት

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 173079 ከፍርድ በፊት የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረትን አስመልክቶ የሚሰጥ የእግድ ወይም ንብረት የማስከበር ትዕዛዝ የመያዣ መብትን የማያቋቁም በመሆኑ የቅድሚያ መብትን ሊፈጥር እንደማይችል አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡ ይህ የህግ ትርጉም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰበር ሰሚ ችሎት ከዚህ በፊት በሰ/መ/ቁጥር 97206 እና በሰ/መ/ቁጥር 29269 በዚሁ ጉዳይ ላይ ሰጥቶት የነበረውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም አሻሽሏል ወይም ለውጧል፡፡

Print
18377