/ Categories: CASSATION, 2013, Cassation

ሲቦ አቦ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን እና እነ አቶ አዲሱ በየነ የሰ/መ/ቁጥር 213179

አመልካች በስር ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረበችው ክስ በቡሬ ወረዳ በስቦ አቦ ቀበሌ ውስጥ የሚገኘውንና አዋሳኙ በክስ ዝርዝር ውስጥ የተገለፀውን እና የባለይዞታነት ማስረጃ በልዪ ቁጥር 10980 ያለውን 10.316 ሄክታር  የመሬት ይዞታ 1ኛ ተጠሪ 19 ጥማድ ፤2ኛ ተጠሪ 12 ጥማድ፤  3ኛ ተጠሪ 5 ጥማድ እንዲሁም 4ኛ ተጠሪ 4 ጥማድ መሬት ለአመልካች ኪራይ ከፍለው ሲጠቀሙበት ቆይተው ጊዜው በክስ ከተገለፀው ጊዜ ጀምሮ ኪራይ መክፈል ያቆሙ እና መሬቱንም ለብቻቸው ይዘው የሚገኙ ስለሆነ እንዲለቁልኝ ይወሰንልኝ በማለት አመልክታለች፡፡ ተጠሪዎች በሰጡት መልስም በዚህ ይዞታ ላይ ቤተሰብ አፍርተን ቋሚ ንብረት ተክለንበት ለረጅም ዓመታት እየተጠቀምንበት ነው፡፡ከአመልካች ጋር የመሬት ኪራይ ውልም የለንም፡፡ በይዞታው ለመንግስት ግብር እየገበርን የምንጠቀምብት ነው፡፡የአመልካች መሬት ልኬትም በቀበሌ እና በወረዳ ደረጀ ተቃውሞ እያቀረብን ነው፡፡እንደ ወረዳ  ለመቃብር ቦታ እያንዳንዳችን 10 ሜትር እንድንቆርስ ተነግሮን አመልካች ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ስለዚህ ክሱን አመልካች ከሕግ አግባብ ውጪ ያቀረበችብን ስለሆነ ውድቅ ይደረግልን በማለት ተከራክረዋል፡፡መልካም ንባብ……

Print
7282

Documents to download

  • 213179(.pdf, 838.99 KB) - 582 download(s)