Monday, July 18, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation ቄስ ቀፀላጊዮርጊስ ደስታ እና አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ፅ/ቤት ፤አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር የሰ/መ/ቁጥር 218309 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጀመረው የሁከት ክርክር የሰበር አመልካች ከሣሽ፣ የሰበር አንደኛ ተጠሪ ተከሣሽ፣የሰበር ሁለተኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ አመልካች ግንቦት 2ቀን 2013ዓ/ም በተፃፈ ክሣቸው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር 648 የሚታወቀው ቤት የግል ቤታቸው መሆኑን፤ የቤት ቁጥር 649 ደግሞ የአስተዳደሩ ሆኖ አመልካች የግል ቤታቸው ስለጠበባቸው በኪራይ እንዲሰጣቸው ሕዳር 21ቀን 1985 ዓ/ም ጠይቀው በቃለ-ጉባኤ ተሰጥቷቸው እንዲሁም ቤቱ ወንዝ ዳር በመሆኑ በወንዙ የተወሰደውን የቤቱን ክፍል በራሣቸው ወጪ አድሰው ኪራይ እየከፈሉ በይዞታቸው አድርገው እስካሁን እየተጠቀሙበት መሆኑንና ውል እንዲይዝላቸው ኪራይም እንዲቀበላቸው ሲጠይቁት ይጠብቁ ሲላቸው ከቆየ በኋላ ሚያዚያ 28ቀን 2013ዓ/ም የግል ቤታቸውን ጨምሮ ማሸጉን ዘርዝረው የፈጠረባቸው ሁከት እንዲቆም የቤቱንም ኪራይ እንዲቀበል እንዲወሰንላቸው ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ……… Print 12236 Documents to download 218309(.pdf, 841.66 KB) - 1257 download(s)