/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

በአማጋ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጮራ የጋዝና ኬሚካል ውጤቶች ፋብሪካ፣ሂክማ የፈሳሽ ሳሙና ማምረቻ ኃ/የተ/የቡድን ኢንተርፐራይዝ እና ሌሎች የሰ-መ-ቁ 175155

ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካች የፌ/ከ/ፍ/ቤት በመ.ቁ139054 በ29/5/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ፤ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 172510 በ26/7/11ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ ቅር በመሰኘት በ7/8/11ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረበ ነው፡፡የጉዳዩ አመጣጥ አመልካች በስር የፌ/ከ/ፍ/ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረበው የተሻሻለ ክስ ለከሳሽ በንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/98 መሰረት ለሁለት አይነት የበረኪና ምርቶች ማለትም ለትልቁ ባለ 800 ሚሊ ሊትር SEDEX እንዲሁም ለትንሹ ባለ 300 ሚሊ ሊትር SEDEX በምዝገባ ቁ.LTM/0189/2005 እና LTOW 0186/2005 በቅደም ተከተል የተመዘገበ እና እስከ 28/10/12ዓ.ም ድረስ ጸንቶ የሚቆይ የንግድ ምልክት ምዝገባ ሰርተፍኬት ከኢትዮጵያ አእምሮአዊ ንብረት ጽ/ቤት በ2005ዓ.ም የተሰጠ ሲሆን የንግድ ምልክቶቹ የተመዘገቡት እና ፈቃድ የተሰጠው በቃል እና በስእል(በቅርጽ) (በምስል) ከመሆኑም ባሻገር የቀለም አይነቱ በአዋጁ አንቀጽ 5(2) መሰረት ጥቁር እና ነጭ ነው፡፡ የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ አላማው የተለያዩ እቃዎችን በማምረትና በማከፋፈል ወይም አገልግሎት በመስጠት የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን መልካም ስም እና ዝና ለመጠበቅ እንዲሁም በተመሳሳይ ስራዎች እና አገልግለቶች መካከል ማሳከርን ለማስወገድ እና አንድን ምርት/እቃ ወይም አገልግሎት በቀላሉ ለመለየትና የንግድ ምልክቱ በአገልግሎት ተጠቃሚው (ኮንሲዩመሩ) ላይ ግርታ እንዳይፈጥር ለማድረግ ነው፡፡…………

Previous Article አቶ አህመድ አብዱራህማን ከ ኢልይስ ዲተርጀንት ኢንዱስትሪ ኩባንያ የሰ-መ-ቁ 193292
Next Article ወ/ሮ ትዕግስት ዓለሙ ቢ/አ/ኤ/ካ ኃ/የተ/የግል ማሕበር የጉባ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት፣የጉባ ወረዳ አካባቢ ጥበቃ፣መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ. 161449
Print
18485