/ Categories: CASSATION, 2013, Cassation

በአዲስ አበባ ከተማ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት እና እነ ወ/ሮ ገነት ገ/ማርያም የሰ/መ/ቁ. 209292

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች በሥር የመቃወም አመልካች ሲሆን 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ፤ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ተከሳሾች ነበሩ፡፡ 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 540/4 የሆነ የንግድ ቤት ከመንግስት ተከራይቼ ስጠቀምብት የነበረ ሲሆን ከ3ኛ ተጠሪ ጋር በተደረገ የኮሚሽን የሥራ ውል አማካኝነት በውሉ መሠረት ሲፈጽሙ ከቆዩ በኋላ የአከራይ ተከራይ መመሪያ ሲወጣ የቤቱ ተከራይ ነኝ በማለትና ሀሰተኛ ማስረጃ በማቅረብ በቤቱ ተከራይ የሆኑ ስለሆነ ያደረጉት የኪራይ ውል እንዲፈርስ፣ በኮሚሽን ውሉ መሠረት እንዲፈጽሙና የንግድ ቤቱን እንዲያስረክቡ በማለት በ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ላይ ክስ አቅርበው ክርክር ተድርጎ በክሱ መሠረት የተወሰነ ሲሆን አመልካች በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሠረት የመቃወም አመልካች ሆኖ ወደክርክሩ የገባ ሲሆን የቤቱ አከራይ እኔ ሆኜ እያለ በሌለሁበት የተደረገው ክርክርና ውሳኔ ተገቢ አይደለም፣ የ1ኛ ተጠሪ ውል የፈረሰውም ንግድ ቤቱን ለ3ኛ ተጠሪ ስላከራዩ በተገቢው መንገድ ነው በማለት የተከራከረ ሲሆን የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍድ ቤት ግራቀኙን አከራክሮ 1ኛ ተጠሪ የኮሚሽን ሥራ ውል ለ3ኛ ተጠሪ ሰጡ እንጂ ንግድ ቤቱን ስላላከራዩ የአመልካች መቃወሚያ ተገቢ አይደለም በማለት ቀድሞ የሰጠውን ፍርድ አጽንቷል፡፡ አመልካች ያቀረበውን ይግባኝ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተቀብሎ ካከራከረ በኋላ ውሳኔውን አጽንቷል፡፡መልካም ንባብ……….

Print
10734

Documents to download

  • 209292(.pdf, 1.07 MB) - 775 download(s)