Tuesday, May 20, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation በፌደራል ጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት እና ሆደን የእንስሳት እርባታ ኮፖሬቲቭ የሰበር መዝገብ ቁጥር-253546 ጉዳዩ ካሳን የሚመለከት ሆኖ ክርክሩ የተጀመረው በሱማሌ ክልል የሲቲ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው፡፡ በስር ፍ/ቤት አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ ጥር 23 ቀን 2015ዓ.ም ለሲቲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጻፈ ክስ ተጠሪ በሱማሌ ክልል የተመዘገበ የእንስሳት ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆኑን በመግለጽ ተጠሪ ለሽያጭ ያቀረባቸው በጎች በድሬዳዋ ከተማ ለመሸጥ ፈልጎ የበግ ዋጋ በመቀነሱ በደንባል ወረዳ ቢዮ ኩሉል ለማቆየት በመገደዳቸው ከሀገሪቱ ድንበር 100 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ለግጦሽ በተሰማሩበት አመልካች 258 የሚሆኑ በጎችን ከህግ አግባብ ውጭ የወሰደባቸው መሆኑን በመጥቀስ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ.129430 እንስሳት በተያዙበት ቦታ በሚገኘው ፍርድ ቤት ስልጣን እንዳለው ውሳኔ የሰጠ በመሆኑ እና እንስሳቱ የተያዙበት ቦታ የሚገኘው ፍርድ ቤት የሲቲ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሆኑ ፍርድ ቤቱ የበጎቹን ዋጋ የሰራተኞችን ወጪ ጨምሮ ብር 2,388,486 ከሳ አመልካች እንዲከፍላቸው እንዲወስላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ …. Print 325 Documents to download 253546(.pdf, 839.05 KB) - 54 download(s)