ቢዲኤፍሲ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ድርጅት ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና አቶ በላቸው ጉተማ የሰበር መ/ቁ/206996
ጉዳዩ የሰራተኛ ደመወዝ ክፍያ ጥያቄ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ጅማ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን የአሁኑ አመልካች ላይ ባቀረበው ክስ በአመልካች ድርጅት ውስጥ በቀን 01/07/2000 ዓ.ም ተቀጥሮ በ5000 ሄክታር መሬት ላይ የሚለማ የቡና እርሻ ስራ አስኪያጅ፣ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ የድርጅቱ አማካሪ በመሆን እየሰራሁ እያለ በአሁኑ ሰዓት በኮቪድ በሽታ ምክንያት በችግር ውስጥ መሆኔ እየታወቀ እኔ እስከአሁን መስሪያ ቤት ተገኝቼ ስራ እየሰራሁ እያለ ከታህሳስ ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ ደመወዝ እየተከፈኝ ስላልሆነ የወር ደመወዝ ብር 10,000.00 ጥቅማ ጥቅም ብር 1,500 እስከ ግንቦት ወር 2012 ዓ.ም ያልተከፈለኝ ብር 69,000 የጠበቃ አበል ብር 15% እና ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዲከፍለኝ እንዲወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል፡፡……..
1024
Documents to download
-
206996(.pdf, 857.85 KB) - 103 download(s)