Wednesday, June 4, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation ብርሃን ባንክ አ/ማ እና ብርሃን ባንክ መሠረታዊ የሠራተኞች ማሕበር የሰ/መ/ቁ. 263727 የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ ነበር፡፡ ተጠሪ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ/ም ጽፎ ባቀረበው ክስ አመልካች ድርጅት ለሁሉም ሰራተኞች በሚል በተጻፈ ጥቅማጥቅም የተወሰነ መሆኑ ተገልጾ እያለ የቤት አበል በተለምዶ በጽሕፈት መደብ ላይ ያልሆኑ /non-clericals/ የሚሰሩ ሰራተኞች አልከፍልም ማለቱ የእኩልነት መብት የሚጥስ በመሆኑ የቤት አበል እንዲከፈል እንዲወሰን ዳኝነት ጠይቋል፡፡ አመልካች በሠጠው መልስ ደብዳቤው ለሁሉም ሠራተኞች በሚል የተጻፈው የተለያየ የጥቅማጥቅም ሁኔታዎች የተካተቱበት ስለሆነ ነው፣ በጽሕፈት መደብ ላይ ላልሆኑ ሰራተኞች የቤት አበል ጥቅማጥቅም አልተወሰነም፣ ጥቅማጥቅም ሳይወሰን ክፍያ እንዲፈጸም ዳኝነት ሊጠየቅበት አይችልም፣ በተመሳሳይ የሥራ መደብ ላይ ለሚሰራ ሠራተኞች የተለያየ ጥቅማጥቅም እንዲያገኙ ያልተወሰነ በመሆኑ የእኩልነት መብትን አልተጣሰም፣ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል፡፡መልካም ንባብ… Print 3525 Documents to download 263727(.pdf, 845.46 KB) - 430 download(s)