/ Categories: CASSATION, Cassation

ተወልደ ግደይ የኤሌክትሪክ ኬብል እና ዋየር ፋብሪካ እናየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሰ/መ/ቁጥር 262505

ጉዳዩ ለቅድመ ጥንቃቄ ዕዳን መልሶ የማዋቀር ሥነ ሥርዓትን የሚመለከት ነው፡፡ጉዳዩ የተጀመረው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአመልካች አቤቱታ አቅራብነት ነው፡፡በአመልካች የቀረበው አቤቱታ ይዘትም በአጭሩ ከተጠሪ ጋር ግንቦት 22 ቀን 2003 ዓ.ም እና ነሀሴ 28 ቀን 2011 በተደረገ የብድር አከፋፈል ስምምነት ብር 692,389,514.50 የብድር ገንዘብ ያለበት መሆኑን፤ብድሩ ተከፍሎ የሚያልቀው የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ.ም መሆኑን፤ከዚህ ውሰጥ ብር 419,224,378.70 መክፈሉን፤ ባጋጠመው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት የፋይናንስ እጥረት ያጋጠመው ቢሆንም አሁን የፋይናንስ እጥረት መሰረት የሆነው የጥሬ እቃ አቅርቦት ችግር በመፈታቱ የፋይናንስ ችግሩ በቅርብ የሚቀረፍ መሆኑን እና ይህም በሚዋቀርለት የዕዳ መክፈያ ጊዜ ውስጥ በተጨባጭ ዕዳውን መክፈል የሚያስችለው መሆኑን እንደዚሁም ሌሎች ምክንያቶችን በመዘርዘር ለቅድመ ጥንቃቄ ዕዳን መልሶ የማዋቀር ሥነ ሥርዓት ተፈቅዶለት ዕዳው ተዋቅሮ የሚከፍልበት ጊዜ እንዲሰጠው፤ዕዳው ሊከፈል የሚችልበትን አማራጭ መፍትሄዎች የሚያጠና ለፍ/ቤቱ፤ለአመልካች እና ለተጠሪ እንዲሁም ሌሎች ገንዘብ ጠያቂዎች ድጋፍ የሚያደርግ እና ሪፖርት የሚያቀርብ ባለሙያ እንዲሾም ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…

Print
3902

Documents to download

  • 262505(.pdf, 892.83 KB) - 451 download(s)