/ Categories: CASSATION, Cassation

ትሬድ ፓዝ ኢንተርናሽናል ኃላ/የተወ/የግ/ማህበር እና ቱርክ አየር መንገድ፤ዘመን ባንክ የሰ/መ/ቁ168954

አመልካች ለፍርድ ቤቱ ያቀረበዉ ክስ ይዘትም በአጭሩ፡- ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር በተደረገ የአየር ጭነት ሽያጭ ወኪልነት ዉል መሠረት የሚጠበቅብኝን ግዴታ ባልፈጽም እስከ ብር 6,984,075.00 የሚደርስ፣ እንዲሁም ህዳር 08 ቀን 2007 ዓ.ም በተደረገ የፖስታ አገልግሎት ዉል የገባሁትን ግዴታ ባልፈጽም እስከ ብር 300,000.00 የሚደርስ 2ኛ ተከሳሽ የባንክ ዋስትና ሰጥቷል፡፡ ከሳሽ በሁለቱም ዉሎች የሚጠበቅብኝን ግዴታ ተወጥቼ እያለሁ ከፖስታ አገልግሎት ዉል ጋር በተያያዘ የተፈጠረን የሂሳብ ልዩነት በተመለከተ በዉይይት ላይ እያለን 1ኛ ተከሳሽ 2ኛ ተከሳሽ በሰጠዉ ዋስትና መሠረት ብር 6,984,075.00 እንዲከፍለዉ የጠየቀዉ ሲሆን፣ 2ኛ ተከሳሽም የተጠየቀዉን ገንዘብ ለ1ኛ ተከሳሽ ከፍሎ በኋላ እንደሚጠይቀኝ አሳዉቆኛል፡፡ ይሁንና ይህ የብር 6,984,075.00 ዋስትና የተሰጠዉ ለአየር ጭነት አገልግሎት እንጂ ለፖስታ አገልግሎት ካለመሆኑም በላይ ክፍያዉን 2ኛ ተከሳሽ የሚፈጽመዉ ከሆነ በከሳሽ መልካም ስም ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር እና ከባንኮች የምፈልገዉን አገልግሎት ለማግኘት እንቅፋት የሚፈጥርና ከተሰማራሁበት ንግድ አንፃር ሊተካና ሊካካስ የማይችል ጉዳት የሚያደርስብኝ በመሆኑ 2ኛ ተከሳሽ ገንዘቡን ለ1ኛ ተከሳሽ መክፈል የለበትም ተብሎ ይወሰንልኝ የሚል ነዉ፡፡ ተጠሪዎች በየበኩላቸዉ ባቀረቡት መልስ፣ በ2ኛ ተከሳሽ ለ1ኛ ተከሳሽ የተሰጠ የዋስትና ሰነድ ከዋናዉ ዉል ተለይቶ የቆመ እና ያለ ቅድመ ሁኔታ ጥያቄ ሲቀርብ የሚከፈል የዋስትና ዓይነት መሆኑን ጠቅሰዉ የቀረበባቸዉ ክስ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተመሳሳይ ይዘት ያለዉ ክርክር አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ…

Print
1899

Documents to download

  • 168954(.pdf, 830.42 KB) - 239 download(s)