Wednesday, June 4, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation ቻይና ኮሙኒኬሽን ኩባንያ ግንባታ ወንጪ ደንዲ ኢኮቱሪዝም ፕሮጀክት እና ማንዴሳ ጪብሳ የሠ/መ/ቁጥር 256412 ጉዳዩ የጉዳት ካሳ ክፍያን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ደግሞ በተከሳሽነት ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ፡- አመልካች ከደንዲ ሀይቅ እስከ ወንጪ ሀይቅ ያለው መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ኮንትራክተር በመሆን በሚሰራበት ወቅት በደንዲ ወረዳ ገ/ጥራንጉ ሹቤሶሌ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከሚገኘው ስፋቱ አራት ሄክታር በሆነው የእርሻ ይዞታዬ ላይ መንገድ ለመገንባት የቆፈረውን አፈር ጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም በተሸከርካሪዎች ጭኖ በመድፋት በመሬቱን ገደላማ በማድረግ ከጥቅም ውጪ በመሆኑ በመሬቱ ላይ ተዘርቶ የነበሩትን የሰነፍ ቆሎ፤ገብስ እና ሚስር ቡቃያዎችን፤ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ በቁጥር 5,900.00(አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ባህር ዛፍ፤10 እግር ጥድ፤እንዲሁም 900 እግር ቀርከሃ ስላወደመብኝ የእጽዋቶቹ እና የሰብል ግምቱ ለወደፊት ያገኙ የነበረውን የ15 አመት ጥቅም በድምሩ ብር 9,823,000 (ዘጠኝ ሚሊየን ስምንት መቶ ሃያ ሶስት ሺ) የጉዳት ካሳ ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዲከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ከሰዋል፡፡መልካም ንባብ… Print 2912 Documents to download 256412(.pdf, 876.52 KB) - 356 download(s)