Thursday, May 29, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አማኑኤል ያዘዉ ተፈሪ እና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 265504 አመልካች በቀን 26/09/2016 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉ ከላይ በተመለከተዉ መሠረት በተሰጠ የጥፋተኝነትና የቅጣት ዉሳኔ ላይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን ይዘቱም በአጭሩ ጫማዎቹን ለሕዝብ ግልጽ ከሆነ ገበያ ቦታ ላይ ገዝቼ ለቤተሰቦቼና ለጎረቤት ልጆች ለመለገስ የገዛሁት እንደሆነና ከዉጭ አገር እንዳላስገባሁ በመከላከያ ማስረጃዎቼ አስረድቼ እያለሁ ጥፈተኛ መባሌ ሕጉን ያልተከተለና የማስረጃ ምዘና ስህተት የተፈጸመበት ነዉ፡፡ባቀረብኩት ሦስት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች መሠረት መቀጣት የሚገባኝ በእርከን 11 ስር በአንድ ዓመት ከስምንት ወር መሆን ሲገባ ሁለት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ከተያዙለት ከስር 2ኛ ተከሳሽ ጋር እኩል በ2(ሁለት) ዓመት ጽኑ እስራት እንድቀጣ መወሰኑ ስህተት ነዉ፡፡እንዲሁም ለአባይ ግድብ 3 ጊዜ ቦንድ መግዛቴ፣ሁለት ጊዜ ደም በመለገስ በጎ አድራጎት ሥራ መፈጸሜ እና ለአረንጋዴ አሻራ ልማት የሚሰማሩ ሰዎችን በራሴ መኪና በማመላለስ ላበረከትኩት አስተዋጽኦ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 86 መሠረት የቅጣት ማቅለያ ተደርጎ እንዲያዝልኝ የጠየቅሁት ሳይያዝልኝ መታለፉ ስህተት ስለሆነ እንደልዩ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ተይዞ ተሻሽሎ ይወሰንልኝ በማለት አመልክቷል፡፡መልካም ንባብ… Print 2997 Documents to download 265504(.pdf, 1.05 MB) - 387 download(s)