/ Categories: CASSATION, Cassation

አባይነሽ አበበ እና የህጻን ዩሃንስ ሃብታሙ ቻይና ሞግዚትና አስተዳዳሪ የሰ/መ.ቁ. 255765

የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች በ27/03/2016 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 93464በ ቀን 22/10/2015 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.308887 በቀን 12/02/2016ዓ.ም ማጽናቱ መሰረታዊ የህግ አተረጓጎም ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለታቸው ሲሆን በስር ፍ/ቤት የአሁን አመልካች ሆነው ተጠሪም ተጠሪ ሆነው የልጅነት ውሳኔ ይሰረዝልኝ በሚል ጉዳይ ተከራክረዋል፡፡

በስር ፍ/ቤት አመልካች በቀን 19/08/2015 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የመቃወምአቤቱታ ሟች ልጃቸው አቶ ሃብታሙ ቻይና ታሞ አልጋ ላይ ባለበት ልጅ ካለው፣ እዳ ካለበት እና የጀመረው እቁብ ካለ እንዲነግራቸው ጠይቀውት የሌለው መሆኑን ተናግሮ ከሞተ በኋላ የተጠሪ ሞግዚት ህጻኑ የሟች ልጅ ነው በማለት ያሰጡት ውሳኔ ተገቢነት የሌለው በመሆኑ የተጠሪ እና የሟች የዘረ መል ምርመራ ተደርጎ የተሰጠው ውሳኔ እንዲሻርላቸው ጠይቀዋል፡፡

ተጠሪም በቀን 18/09/2015 ዓ.ም በተጻፈ መልስ የመካድ ክስ ማቅረብ የሚችለው አባት የሆነ ሰው ብቻ በመሆኑ አመልካች ይህን ክስ ለማቅረብ መብት የላቸውም፡፡ መብት አላቸው ቢባል እንኳ ክሱ ሊቀርብ የሚገባው ህጻኑ መወለዱ ከታወቀበት ወይም መወለዱ መታወቅ ከሚገባው ቀን ጀምሮ በ180 ቀን ውስጥ ሊሆን ሲገባ አመልካች የህጻኑን መወለድ እያወቁ በዚሁ የጊዜ ገደብ ክስ ያላቀረቡ በመሆኑ ክሱ በይርጋ የሚታገድ ነው የሚል መቃወሚያ ከፍሬ ነገር ክርክር ጋር አቅርበዋል፡፡ መልካም ንባብ ….

Print
439

Documents to download

  • 255765(.pdf, 832.49 KB) - 100 download(s)