Tuesday, March 9, 2021 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation አቶ ሀበን ግዑሽ እና ሊቢያ ኦይል ኢትዮጵያ ሊሚትድ የሰ-መ-ቁ. 188331 የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች ተከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪ ከሳሽ ነበር፡፡ ተጠሪ ያቀረበው ክስ ከአመልካች ጋር ጥቅምት 25 ቀን 2002 ዓ/ም፣ መጋቢት 10 ቀን 2002 ዓ/ም፣ ሕዳር 12 ቀን 2004 ዓ/ም፣ ሀምሌ 30 ቀን 2004 ዓ/ም፣ ሕዳር 21 ቀን 2005 ዓ/ም እና ሕዳር 21 ቀን 2005 ዓ/ም የነዳጅ ማደያ ጣቢያ ኦፕሬተር/ዲለር ሥምምነቶች ተደርጓል፡፡ አመልካች የነዳጅ ውጤቶችን በጅምላ እየገዙ በሽሬ ከተማ፣ ሞጆ ከተማ፣ ዳንሻ ከተማ፣ ሁመራ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ ሁለት ቦታ ላይ ባሉ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች ለመቸርቸርና የማደያ ጣቢያ አገልግሎት ለመስጠት ግዴታ ገብተዋል፡፡ አመልካች የተረከቧቸውን የነዳጅ ውጤት ምርቶችን ባለመክፈላቸው በተለያዩ ጊዜያት ዕዳ ተሳስበን የሚከፍሉበት ጊዜ ተወስኗል፡፡ ክፍያ በማቋረጣቸውም ጥር 23 ቀን 2008 ዓ/ም በተደረገ 3ኛ የውል ማሻሻያ ሥምምነት በ2ኛው የውል ማሻሻያ ከተመለከተው ያልተከፈለው ብር 24,275,805.86 በየወሩ ብር 1,391,255.80 ሊከፍሉና ተጨማሪ አመልካች በዱቤ ሽያጭ የተረከቧቸውን ምርቶች ዋጋ ብር 8,816,151.10 በየወሩ ብር 367,339.63 ከፍለው ሊያጠናቅቁ የተስማማን ሲሆን ጎን ለጎን ሥራውን እንዲሰሩ፣ ወርሃዊ ዕዳ አከፋፈል የጊዜ ሠሌዳ ባያከብሩ በ3ኛው የውል ማሻሻያ ሥምምነት አንቀጽ 6 እና 2.13 እንዲሁም በስድስቱ የኦፕሬተር/ዲለር ውሎች አንቀጽ 5.3፣ 12፣ 13 እና 14 መሠረት ውሎችን የማቋረጥና ዕዳውን አጠቃሎ የማስመለስ መብት እንዳለን ተመልክቷል፡፡ አመልካች ለሠባት ተከታታይ ወራት ምንም ክፍያ አልከፈሉም፡፡ አራት ቼኮች ዋጋቸው ብር 27,902,795.60 የሆኑ የሠጡ ቢሆንም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቂ ስንቅ ስለሌላቸው ክፍያ ሊፈጸም አለመቻሉን ገልጾ ቼኮቹን መልሷል፡፡ ለአመልካች ክፍያውን እንዲፈጽሙ ግንቦት 01 ቀን 2008 ዓ/ም ማስጠንቀቂያ የተሠጣቸው ቢሆንም አልከፈሉም፤ የውል ግዴታቸው ጥሰው ከስድስት ወራት በላይ ማደያዎች አገልግሎት ሳይሰጡ ያለስራ እንዲቆዩ አድርገዋል፡፡ ስለዚህ በ3ኛው የውል ማሻሻያ ሥምምነት መሠረት ብር 33,091,956.96 ከሕጋዊ ወለድ ጋር አመልካች ለተጠሪ እንዲከፍሉ እንዲወሰን ዳኝነት ጠይቋል፡፡……….. Previous Article አቶ ፍቃዱ አዱኛ እና የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የጠበቆች የዲስፕሊን ጉባኤ የሰ-መ-ቁ-195138 Next Article እነ ወ-ሮ ብርሃን ገ/መድህን እና የሐውዜን ከተማ ማዘጋጃ ቤት የሰ-መ-ቁ 182677 Print 14023 Documents to download አቶ ሀበን ግዑሽ እና ሊቢያ ኦይል ኢትዮጵያ ሊሚትድ የሰ-መ-ቁ. 188331(.pdf, 786.92 KB) - 1327 download(s)