/ Categories: CASSATION, Judgement, Cassation

አቶ ሀብታሙ ዝናቡ እና አቶ ታሪኩ አየለ የሰ/መ/ቁ 196871

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ የከተማ ይዞታ ክርክርን የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/333779 ላይ ጥቅምት 03/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔን በማፅናት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት ለማስለወጥ ነው፡፡

ክርክሩ የተጀመረው የአሁን ተጠሪ ሐምሌ 05/2011 ዓ.ም ፅፈው በአሁን አመልካች ላይ በጅማ ወረዳ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ነው፡፡ ፍሬ ቃሉም ቦታ እና አዋሳኙ በክሱ ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሰውን 200 ካሬ ሜትር የከተማ ይዞታ ነሐሴ 06/2011 ዓ.ም ተሰጥቷቸው አስፈላጊውን ክፍያ ፈፅመው እና የግንባታ ፈቃድ አውጥተው በቦታው ላይ ግንባታ ለማከናወን ሲሄዱ ባላወቁት መንገድ የአሁን አመልካች ትንሽ ሰርቪስ ቤት ሰርተዉበት የያዙባቸው መሆኑን በመግለፅ በፍርድ ኃይል ተገደው በቦታው ላይ የሰሩትን ቤት አፍርሰው እንዲለቁላቸው ዳኝነት የሚጠይቅ ነው፡፡……………

Previous Article አቶ በፍቃዱ ጌታቸው እና እነ አቶ ዮናስ ጌታነህ የሰ/መ/ቁ196346
Next Article አቶ ኃይለጊዮርጊስ ይልማ እና አቶ አዲስ እሸቱ የሰ/መ/ቁጥር 197009
Print
18451

Documents to download

  • 196871(.pdf, 809.67 KB) - 1158 download(s)