Friday, March 4, 2022 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ ሁሴን ሙክታር እና እነ ወ/ሮ ብዙነሽ ፋፋ የሰ/መ/ቁ፡- 212313 ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ ሊቀርብ የቻለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በይ/መ/ቁ.275565 በቀን 28/11/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የስር የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት አመልካች በምዕራብ በኩል 1 ሜትር ወደ ተጠሪዎች ይዞታ በመግባት በመያዝ የፈጠረው ሁከት ሊወገድ ይገባል በማለት የሰጠውን ውሳኔ በማፅናት ብይን መስጠቱ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት በመሆኑ ይኸው ስህተት እንዲታረምልኝ በማለት አመልካች ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ መነሻ በማድረግ ሲሆን አመልካች በፌደራል የመጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት 2ኛ ተከሳሽ የነበሩ ሲሆን ተጠሪዎች ከሳሾች ነበሩ፡፡ ተጠሪዎች በስር ፍርድ ቤት በአመልካች እና በስር 1ኛ ተከሳሽ ላይ ባቀረቡት ክስም በን/ስ/ላ/ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 የቤት ቁጥር ኮድ 44 የሆነ በ180 ካሜ ላይ ያረፈ የመኖሪያ ቤት ከሟች ባለቤቴ አቶ ታረቀኝ አላምረው ጋር በመሆን ነሀሴ 04 ቀን 1991 ዓም በተደረገ የሽያጭ ውል ከአቶ አረብሳ ማሞ እና ወ/ሮ መስታወት ሀይሌ በመግዛት ተረክበን ስንኖር አመልካች በስተምዕራብ በኩል ወደ ይዞታችን ጥሶ በመግባት ህገወጥ ግንባታ የፈፀመ እና በጥር ወር 2011 ዓም አጥር በማፍረስ ሁከት የፈጠረብን በመሆኑ ይዞታችንን ለቅቆ እንዲያረክበን ይወሰንልን በማለት አመልክተዋል፡፡……… Print 10892 Documents to download 212313(.pdf, 817.97 KB) - 906 download(s)