Friday, December 31, 2021 / Categories: CASSATION, Judgement, Cassation አቶ ሆርዶፋ ዴቲ እና ወ/ሮ ፀሐይ ሽፈራው የሰ/መ/ቁ፡-201929 ጉዳዩ የፍርድ አፈፃፀም ክስ መነሻ ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው ኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን 1ኛ ተጠሪ የአፈጻጸም ከሳሽ፤የአሁኑ አመልካች በአፈጻጸም ተከሳሽ፤የአሁኑ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ደግሞ ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል፡፡የክርክሩ አመጣጥ ባጭሩ ሲታይ አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ ጋብቻቸው በፍቺ እንዲፈርስ ከተወሰነ በኋላ 200 ሄክታር የቡና ልማት የኢንቨስትመንት ይዞታ የጋራ ንብረት ነዉ ተብሎ እኩል እንዲካፈሉ ተወስኖ የፌዴራል ፍ/ቤቶች የአፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ንብረቱ ያለበት የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በውክልና ውሳኔውን እንዲያስፈጽም ትዕዛዝ መስጠቱን ተከትሎ የአፈፃፀም መዝገብ ቁ/42899 ተከፍቶ በሂደት ላይ እያለ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በየበኩላቸዉ ባልና ሚስቱ ከባንኩ ተበድረዉ ያልከፈሉት እዳ መኖሩን በተለያየ መዝገብ ያሰጡትን ፍርድ በማቅረብ ንብረቱ በባልና ሚስት መካከል ክፍፍል ከመደረጉ በፊት እዳዉ እንዲከፈላቸዉ አቤቱታ በማቅረብ የክርክሩ ተካፋይ መሆናቸዉን መዝገቡ ያሣያል፡፡………………. Previous Article ወ/ሮ መሠረት ኃይሉ እና ወ/ሮ ቢቂልቱ በየነ የሰ/መ/ቁ. 201128 Next Article አቶ ታደሰ ንጉሴ እና አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ሻሸመኔ ቅርንጫፍ የሠ/መ/ቁጥር 201974 Print 17394 Documents to download 201929(.pdf, 558.52 KB) - 1356 download(s)