/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ መሐመድ አሊይ ገዳሊ እና ወ/ሮ ቀቡላ አልይ ኡስማን፤ ወ/ሮ ቢፍቱ አልይ ኡስማን የሰ/መ/ቁ 250349

ለዚህ የሰበር ክርክር ምክንያት የሆነዉ ጉዳይ የተጀመረዉ በሐረማያ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን በወረዳዉ ፍርድ ቤት አመልካች ተከሳሽ ተጠሪዎች ደግሞ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪዎች በሐረማያ ወረዳ ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ አመልካች የተጠሪዎችን እህት በማግባቱ ካላቸዉ  የጋብቻ  ዝምድና የተነሳ ወላጅ  አባታቸዉ ሟች አቶ አልይ ኡስማን   

በሕይወት በነበሩ ጊዜ በ1998 ዓ/ም ለዚህ የሰበር ክርክር ምክንያት የሆኑትን ሁለት የገጠር እርሻ መሬት ይዞታዎችን እኩል እንዲያርስ ሰጥተዉት እስከ ዕለተ ሞታቸዉ ድረስ ምርቱን እኩል ሲጠቀሙ ቆይተዉ ከሞቱ በኋላ ወራሽነታቸዉን አረጋግጠዉ መብታቸዉን እንዲጠብቅላቸዉ ቢጠይቁትም ከልክሏቸዉ ለብቻዉ እየተጠቀመ ስለሚገኝ ይዞታዉን እንዲለቅላቸዉ በሀገር ሽማግሌዎች ቢያስጠይቁትም እንቢተኛ ሆኖ ስለተገኘ ከሁለቱ ይዞታዎች በአንደኛዉ ላይ ከፈቃዳቸዉ ዉጭ የሠራዉን ሰባት ክፍል ቤት በራሱ ወጪ አፍርሶ ይዞታዉን እንዲለቅ እንዲወሰንላቸዉ ዳኝነት በመጠየቅ ክስ አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ…

Print
2089

Documents to download

  • 250349(.pdf, 830.25 KB) - 269 download(s)