Monday, June 6, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation አቶ መብሬ ይማም እና ወ/ሮ ደስታ ግርማ የሰበር መዝገብ ቁጥር 206006 የደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት በመዝገብ ቁጥር 50715 የሰጠው ትዕዛዝ እንዲሁም የወግድ ወረዳ ፍርድ ቤት መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠውን ብይን በመቃወም አመልካች ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር አጣሪው ችሎት ሚያዝያ 1 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት በመዝገብ ቁጥር 0332446 በመሰረዝ የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት አመልካች ሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ/ም ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ መዝገቡ ለችሎት ሊቀርብ ችሏል፡፡ ጉዳዩ የግራ ቀኙን ክርክር ለመስማት በተቀጠረበት ዕለት የሥር ተከሳሽ የሆኑት አመልካች ባለመቅረባቸው ክርክሩ በሌሉበት እንዲቀጥል የተሰጠ ብይን እንዲነሳ አመልካች ያቀረቡት አቤቱታ በየደረጃው ባሉት የሥር ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት በማጣቱ የቀረበ የሰበር አቤቱታን የሚመለከት ሲሆን ፤ ክርክሩ በተጀመረበት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የወግድ ወረዳ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ ሲሆኑ አመልካች ተከሳሽ ነበሩ፡፡ አመልካች በተጠሪ ለቀረበባቸው ክስ በሰጡት መልስ ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ በቀጣዩ ቀጠሮ ብይን ተሰጥቶ ክሱን ለመስማት በተያዘው ቀጠሮ አመልካች ባለመቅረባቸው በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 70(ሀ) መሰረት ጉዳዩ አመልካች በሌሉበት እንድታይ በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት የሥር ከሳሽ የአሁን ተጠሪ ክርክር አመልካች በሌሉበት ተሰምቶ መዝገቡን መርምሮ ተገቢውን ጭብጥ ለመመስረት በተያዘው ቀጠሮ አመልካች ክርክሩ በሌሉበት እንዲታይ የተሰጠው ብይን እንዲነሳ ያቀረቡት አቤቱታ ይዘት፡- እንደሚከተለው ቀርቧል…….. Print 11077 Documents to download 206006(.pdf, 828.61 KB) - 1113 download(s)