/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

አቶ ረዲ አህመድ እና ወ-ሮ መኪያ ሀሰን የሰ-መ-ቁ 175719

ይህ የባልና ሚስት የንብረት ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.223910 በ10/8/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ። የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የነበረዉ ጋብቻ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍ/ቤት በሰጠዉ ዉሳኔ ጋብቻችን በፍቺ እንዲፈርስ ወስኗል። ስለሆነም አመልካች እና ተጠሪ በጋራ የፈራነዉ በሱሉልታ ከተማ ልዩ ስሙ ድሬ ጀርባ የሚገኘዉ የቤት ቁጥር 632 SUL 2.1 የሆነዉ በተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የመኖሪያ ቤት እንዲንካፈል እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል። የአሁን ተጠሪ በዚህ ክስ ላይ ባቀረቡት መልስ ይህን ቤት ተጠሪ ከአመልካች ጋር የነበረን ጋብቻ ከተቋረጠ በኋላ ተጠሪ ከግለሰብ ገንዘብ ተበድሬ የተሰራ ስለሆነ የጋራ ንብረት ሳይሆን የግል ንብረቴ በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል።………

Previous Article እነ ወ/ሮ አያልነሽ ፈንቴ እና ወ/ሮ ብርሃኔ ተካ የሰ-መ-ቁ182110
Next Article እነ ወ-ሮ ጀማነሽ ቀነኒ፣አቶ አሰፋ ሸቡ እና ወ-ሮ ብርቱካን ሸቡ የሰ-መ-ቁጥር 177205
Print
13635

Documents to download