Wednesday, June 4, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ ሰለሞን አርአያ እናእነ ህፃን ዳንኤል ቴውድሮስ ሞግዚት ወ/ሮ የሺ መንግስቱ(5ሰዎች)የሰ/መ/ቁጥር፡- 255592 ጉዳዩ የውርስ ማጣራትን የሚመለከት ሆኖ አቤቱታው በቀረበበት የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት አመልካች 5ኛ ጣልቃ ገብ ፣ 2ኛ ተጠሪ የስር ተጠሪ፤1ኛ ተጠሪ የስር አመልካች፤ ከ3ኛ እስከ 5ኛ ያሉ ተጠሪዎች ደግሞ 3ኛ፤4ኛ እና 6ኛ ጣ/ገቦች ነበሩ፡፡ የክርክሩ አመጣጥ በአጭሩ፡- የአሁን 1ኛ ተጠሪ ባቀረቡት አቤቱታ የሟች ባለቤታቸው ቴውድሮስ አርአያ ወላጆች የልጃቸው አያት የሆኑት ጀነራል አርአያ ዘርዓይ ጥር 25 ቀን 2003 ዓም እናቱ ወ/ሮ ሰነዳይ ሀይሌ ጥር 04 ቀን 2004 ዓም ከዚህ አለም በሞት የተለዩ መሆኑን፤ባለቤታቸው ከወንድሞቹና እህቶቹ ጋር በመሆን በ29/08/2005 ዓም ወራሽነታቸውን ያረጋገጡ ቢሆንም ውርሱ ሳይጣራ መኖሪያ ቤቱን ሳይከፋፈሉ በጋራ ይዘው ሲጠቀሙበት ቆይተው ከ2006 ዓም ጀምሮ ቤቱን አከራይተው የኪራዩን ገንዘብ እኩል እየተካፈሉ መሆኑን ገልጠው ድርሻቸውን ለይተው ለማወቅና ለማረጋገጥ እንዲችሉ የውርስ ሀብት እንዲጣራ ጠይቀዋል፡፡ መልካም ንባብ….. Print 3540 Documents to download 255592(.pdf, 834.83 KB) - 521 download(s)