Tuesday, May 27, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ ሰንበቶ ዶጊሶ እና ወ/ሮ ብዙነሽ የኋላሸት የሠ/መ/ቁጥር 255911 ጉዳዩ የጋብቻ ፍቺ በንብረት ረገድ የሚያስከትለዉን ዉጤት ለመወሰን የዳኝነት ሥልጣን የሚኖረዉን ፍርድ ቤት የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች በተጠሪ ላይ በመሠረቱት ክስ - በአመልካችና በተጠሪ መካከል የነበረው ጋብቻ በዚሁ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 3197 ላይ በቀን 03/02/2015 ዓ.ም በተሰጠው ዉሳኔ ፈርሷል፡፡ በጋብቻ በቆየንበት ወቅት ያፈራነዉ የጋራ ሀብት የሆነ በአዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ በይዞታ መለያ ቁጥር 000060602004 የተመዘገበ ስፋቱ 203 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ የመኖሪያ ቤት እና 3 ክፍል ሰርቪስ ቤት አለን፡፡ እንዲሁም የቤት ዕቃዎች ቁምሳጥን ከነዕቃው፣ፍሪጅ፣የኮካ ሳጥን በቁጥር 2፣የሚሪንዳ ሳጥን በቁጥር 2 የጊዮርጊስ ቢራ ሳጥን አለን፡፡ በመሆኑም ተጠሪ እነዚህን ንብረቶች እንዲያካፍሉኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ መልካም ንባብ… Print 1914 Documents to download 255911(.pdf, 1.07 MB) - 293 download(s)