/ Categories: CASSATION, 2013, Cassation

አቶ ሲሣይ መሌ እና የን/ላ/ክ/ከተማ መሬት ልማትና ማኔ/ የሰነድ አልባ መስተንግዶ ፕ/ፅ/ቤት የሰ/መ/ቁጥር 210526

ክርክሩ በተጀመረበት የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች ከሳሽ የአሁን ተጠሪ ደግሞ ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ አመልካች ሚያዚያ 14ቀን 2011ዓ/ም በተፃፈ ክሱ አቶ ቸኮል አዳነ ጋር በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ክልል ውስጥ ስፋቱ 354.88 ካሬ ሜትር በሆነ ይዞታ ላይ የተሰራ ቤት መግዛታቸውንና በከተማው መመሪያ ቁጥር 12/2004 በሚፈቅደው መሰረት ለሁለት መካፈላቸውን፤ አመልካች ድርሻው በሆነው 173.44 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ መብት እንዲፈጥርለት ለተጠሪ ጥያቄ አቅርቦ  ካርታ ሰርቶ የሰጠውና የሊዝ ውል ገብቶ ክፍያ ሲከፍል ከቆየ በኋላ ካርታው ከአቶ ቸኮል አዳነ ይዞታ ጋር የተደራረበ (overlap) አድርጓል፣ ከመንገድ የሚዋሰነው የይዞታው ጎንም (frontage) ከስታንዳርዱ በታች ነው በሚል ምክንያት ተጠሪ የሰጠውን ካርታ ተመላሽ እንዲሆንና እንዲሰረዝ በማድረግ የመንገድ አዋሳኝ ጎኑ ርዝመት 7 ሜትር ለማይሞላው ለአቶ ቸኮል አዳነ ይዞታ ካርታ ሰርቶ መስጠቱን፣ የአመልካች ይዞታ ከመንገድ የሚዋሰነው ጎን (frontage) ርዝመቱ ስድስት ሜትር ቢሆንም በመመሪያ ቁጥር 12/2004 አንቀፅ 19 (1) (2) በሚደነግገው መሰረት ካርታ ከማግኘት የማያግድ መሆኑን በመዘርዘር ተጠሪውን ከመመሪያው ውጪ የሰረዘበትን ካርታ እንዲመልስለት እንዲወሰንበት ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ……….

Print
11635

Documents to download

  • 210526(.pdf, 1.03 MB) - 943 download(s)