Thursday, July 21, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation . አቶ ሲሳይ ለገሰ ቡሩሳ እና ወ/ሮ እቴነሽ ተስፋዬ የሠ/መ/ቁጥር 211615 ጉዳዩ ዉል ለማስፈረስ የተጠየቀ ዳኝነት ተከትሎ የተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ተብሎ የቀረበ የሰበር አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡ተጠሪ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ቤት በአሁን አመልካችና በስር 1ኛ ተከሳሽ ተሾመ ተስፋዬ ላይ በመሰረቱት ክስ አዋሳኞቹ በክሱ የተጠቀሰዉን በመከጡሪ ከተማ ዉስጥ ያላቸዉን ወላጅ አባታቸዉ አቶ ተስፋዬ ጨቡዴ እና እናታቸዉ ወ/ሮ አበራሽ ወርቁ በቀን 30/01/1992 ዓ/ም በተጻፈ ዉል አዋሳኙ በክሱ ላይ በተጠቀሰዉ ይዞታ ላይ የተሰራዉን መኖሪያ ቤት ለወንድማቸዉ ለስር 1ኛ ተከሳሽ ሲሰጡ 150 ካሬ ሜትር ቦታ ደግሞ ለእሳቸዉ ሰጥተዋቸዉ በቦታዉ ላይ 5 ክፍል ሰርቪስ ቤት መስራታቸዉን፤ ከዚህ በኋላ በ1998ዓ/ም ዉስጥ በግድያ ወንጀል ተከሰዉ ተፈርዶባቸዉ 9ዓመት ከ1 ወር ከታሰሩ በኋላ በዚሁ በሰሩት ክፍል ቤቶች ዉስጥ እየኖሩ እያሉ የስር 1ኛ ተከሳሽ የራሳቸዉን መኖሪያ ቤት ለአመልካች ሲሸጡ የተጠሪንም ሰርቪስ ቤቶች ቀላቅለዉ ሽጠዋል፡፡ስለሆነም በአመልካችና በስር 1ኛ ተከሳሽ መካከል በቀን 06/07/2008ዓ/ም የተጠሪን ሰርቪስ ቤቶች ተጨምሮ የተደረገዉ የሽያጭ ዉል እንዲፈርስ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…….. Print 13378 Documents to download 211615(.pdf, 1.06 MB) - 1015 download(s)