Friday, May 23, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ ሳሙኤል አሊ/ እና እነ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማት ማኔጅመንት መምርያ /ቁ.2 /የሰበርመ/ቁ/259880 ለፍርዱ መነሻ የሆነው ክርክር ከይዞታ ጋር የተያያዘየካሳ ጥያቄንመሰረት ያደረገ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአሶሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የተጀመረ ሲሆን የአሁን አመልካችከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪደግሞ ተከሳሽነበሩ፡፡አመልካች በስር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ በአጭሩ፡-አመልካች በአሶሳ ከተማ ወረዳ 2 ቀጠና 2 ልዩ ስሙ ግብርና ሰፈር በሚባለው አከባቢ 10,000 (አስር ሺህ ) ካ.ሜ ይዞታ ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ በእጄ አድርጌ የምጠቀምበት ያለዉና በይዞታዉ ላይየብር 1,600,000/አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ብር) የሚገመት ባህር ዛፍ፣ ማንጎ እና ጋርቭላ ያለው ሲሆን ተጠሪ ካሳ እና ምትክ ቦታ ሳይሰጠኝ ለ3ኛ ወገን አሳልፎ ስለሰጠብኝ ቅድምያ የማልማት መብቴ እንዲጠበቅልኝ፣ ምትክ መሬት እንዲሰጠኝ እና የአትክልቶቹ ካሳ ብር 1,600,000/አንድ ሚልዮን ስድስት መቶ ሺህ/ እንዲከፍል እንዲወሰንልኝየሚልነው፡፡መልካም ንባብ …. Print 2249 Documents to download 259880(.pdf, 845.67 KB) - 296 download(s)