/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

አቶ ቀኖ ኩታሳ እና ወ-ሮ መሳይ ገመቹ የሰ-መ-ቁ 180936

ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካች የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 303340 በ11/10/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት በ11/11/11ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ የአሁን ተጠሪ በስር በጅማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የኖኖ ቤንጃ ወረዳ ፍ/ቤት በአሁን አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ በክሱ 1ኛ እና 2ኛ ተራ ቁጥር ላይ የተጠቀሰው ስፋቱ እና አዋሳኙ የተጠቀሰው አንድ ባር ሳር ቤት ግምቱ ብር 4000(አራት ሺህ ብር) የሚያወጣ አለን፤ በክሱ ከተራ ቁጥር 3  እስከ 47 የተጠቀሱትን ንብረቶች አመልካች ድርሻዬን እንዲያካፍለኝ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀው አመልካች ባቀረቡት መልስ ከተጠሪ ጋር የኖርነው አስር ወር ብቻ ነው፤ ክስ የቀረበባቸውን ንብረቶች ከቀድሞ ሚስቴ ወ/ሮ ያደሺ ያንካ ጋር ከ1990ዓ.ም ጀምረን ያፈራናቸው ንብረቶች ተጠሪን አይመለከትም፤ ተጠሪ ያላት ንብረት የቤት ውስጥ እቃ ብቻ ሲሆን እነሱም በተራ ቁጥር 12፤13፤14፤15፤19፤20፤23፤24፤26፤27 ሲሆኑ ያልተመዘገቡ ንብረቶች ደግሞ በተራ ቁጥር 3፤4፤5፤6፤16፤18፤21፤22፤25፤28፤29፤30፤31፤35፤36፤46 ሲሆኑ በተራ ቁጥር 46 ላይ የተጠቀሰው ኑግ የለም፤ በተራ ቁጥር 6 ላይ የተጠቀሰው በሬ የቀድሞ ሚስቴ ንብረት ነው፤ በተራ ቁጥር 45 ላይ  የተጠቀሰው ንብረት ተጠሪን ሳላገባት በፊት በ2007ዓ.ም ውስጥ ከቀድሞ ሚስቴ ጋር የገዛነው ነው፤ በተራ ቁጥር 1 እና 2 ላይ የተጠቀሰውን ንብረት አመልካችን ሳላገባት በፊት በ2007ዓ.ም ከቀድሞ ሚስቴ ጋር አፍርተን የባለቤትነት ማስረጃ ስላለን ተጠሪን አይመለከትም፤ በተራ ቁጥር 47 ላይ ተጠሪ የገለጸችውን ቤት በ2007ዓ.ም ከቀድሞ ሚስቴ ጋር ያፈራነው ስለሆነ ተጠሪን አይመለከትም፤ በ27/1/10ዓ.ም የተፈጸመው ውል ደግሞ ተጠሪ የገጠሩ ኑሮ አቅቶኛል ወደ ከተማ አስገባኝ ብላ በሽማግሌ ስለጠየቀችኝ ያደረኩት ውል እንጂ የሰጠኋት ስጦታ የለም፤ ስጦታ አልተሰጠም እንጂ ተሰጥቷል ቢባል እንኳን በመካከላችን የነበረውን አለመግባባት ለመፍታት የተፈጸመ ውል ስለሆነ ውሉ እንዲፈርስልኝ ፤ በ29/8/09ዓ.ም የተፈጸመውን ውል ደግሞ የቀድሞ ሚስቴን ሳላማክራት የፈጸምኩት ውል ስለሆነ  ከቤተሰብ ህጉ የሚቃረን ውል ስለሆነ ውድቅ እንዲደረግልኝ በማለት የተከራከሩ ሲሆን፤  በስር ጣልቃ ገብ የሆኑት ወ/ሮ ያደሺ አንካ (አሁን በሰበር አቤቱታው ላይ የሌሉ) በጣልቃገብነት ገብተው እንዲከራከሩ ተፈቅዶላቸው ባቀረቡት አቤቱታ ከአመልካች ጋር በ1990ዓ.ም ጋብቻ መስርተን አንድ ልጅ እና ንብረት አፍርተን እያለ አመልካች እና ተጠሪ ጋብቻ ፈጽመው ጋብቻቸውን አፍርሰው ወደ ንብረት ክርክር ሲሸጋገሩ ተጠሪ ከአመልካች ጋር ለአስር ወራት ብቻ የኖረች ሲሆን በተራ ቁጥር 1፤2፤6፤7፤8፤9፤10፤11፤31፤32፤33፤34፤37፤38፤39፤40፤41፤42፤43፤44፤45፤47 ላይ ተጠሪ የጠቀሰችው ንብረት እኔ ያፈራሁት ንብረት ስለሆነ ከክርክሩ ይውጣልኝ፤ በ29/8/10ዓ.ም የተደረገውን  የስጦታ ውል በተመለከተ አመልካች ከጣልቃገብ ፍላጎት ውጪ የጋራ ንብረታችን የሆነውን ለ3ኛ ወገን ለማስተላለፍ መብት የሌለው በመሆኑ ውሉ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ጠይቀዋል፡፡...............

Previous Article እነ አቶ ጁሀር ያህያ እና ወ/ሮ መሬም አህመድ የሰ.መ.ቁ 179607
Next Article አቶ ደጋረገ ሙሉ እና ወ-ሮ ውብናት ላቀ የሰ-መ-ቁ 181649
Print
14267

Documents to download