Friday, March 4, 2022 / Categories: CALENDARS, Cassation አቶ በሪሁን አጥናፍ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የሰ/መ/ቁ፡-203253 ክርክሩ የተጀመረው የአሁን ተጠሪ አመልካችን ጨምሮ በሶስት ተከሳሾች ላይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1(ሀ)) እና 669(1(ለ)) ድንጋጌን ጠቅሶ በሰሜን አቼፈር ወረዳ ፍ/ቤት ባቀረበው የወንጀል ክስ ነው፡፡ በቀረበው ክስ ውስጥ የአሁን አመልካች 2ኛ ተከሳሽ ነበር፡፡ የክሱም ጭብጥ አመልካች ከስር ፍርድ ቤት 1ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ከነበሩት ጋር በመሆን የተጠቀሰውን የወንጀል ህግ ድንጋጌን ተላልፈው መስከረም 28 ለ29 ቀን 2013 ዓ.ም አጥቢያ ከሌሊቱ 7፡30 ሰዓት አካባቢ የተለየ ጠባቂ የሌለውን እና ለይስማዕላ ከተማ ህዝብ የውሃ አገልግሎት የሚሰጠውን ግምቱ ብር 160,000 (አንድ መቶ ስልሳ ሽህ ብር) የሆነ የውሃ ኮንትሮል ፓኔል ቦርድ ሰርቀው ወስደው በተደረገ ጥቆማ 1ኛ ተከሳሽ የነበረው ተይዞ ወደተከራየው ቤት ሲወሰድ 1ኛ ተከሳሽ ቤቱን እንዲከፍት ሲጠየቅ “ቁልፍ ጠፍቶብኛል” በማለቱ የቤቱ ቁልፍ ተሰብሮ ሲገባ ከአሁን አመልካች እና ከሰር ፍርድ ቤት 3ኛ ተከሳሽ ጋር እቃው በቤቱ ውስጥ የተገኘ በመሆኑ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተሳታፊ በመሆኑን ከባድ የስርቆት ወንጀል ፈፅመዋል የሚል ነው፡፡………… Print 12993