Wednesday, February 23, 2022 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation አቶ በፍቃዱ ጌታቸው እና እነ አቶ ዮናስ ጌታነህ የሰ/መ/ቁ196346 ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካች መስከረም 22 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 182644 ሰኔ 12 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ቅሬታውን በማቅረቡ ነው፡፡ ቅሬታውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካች የሚቃወምባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ሊታይልኝ ይገባል የሚለውን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ ያከራከረን ቤት በእናቴ ስም የተመዘገበ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ ጣልቃ ገብዎች ቤቶቹን ሰራን የሚሉት 1ኛ ጣ/ገብ አያቴ ሞግዚቴ ሆኖ ባለበት ጊዜ መሆኑ እየታወቀ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ያላደረኩትን እርቅ መሰረት አደርጎ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው፡፡…….. Previous Article አቶ ከተማ ኑኔ እና ወ/ሮ መረጠች ለማ የሰበር መ/ቁጥር 191095 Next Article አቶ ሀብታሙ ዝናቡ እና አቶ ታሪኩ አየለ የሰ/መ/ቁ 196871 Print 12563 Documents to download 196346(.pdf, 1.04 MB) - 1016 download(s)