Monday, July 18, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation አቶ ቢኒያም ግርማ ታደሰ እና አቶ ያሬድ በፍቃዱ ሀይሌ የሰ/መ/ቁጥር 214002 አመልካች መስከረም 7 ቀን 2013 ዓ.ም በአጭር ሥነ-ሥርዓት ባቀረቡት ክስ ተጠሪ በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አክስዮን ማህበር አዲሱ ገበያ ቅርንጫፍ በሒሳብ ቁጥር 7000003133678 የተመዘገበን ሒሳብ ለማንቀሳቀስ ካወጡት ቼክ ውስጥ ቁጥሩ ቢቲ3209475 በሆነ ቼክ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺ) እንዲከፈለኝ ሐምሌ 17 ቀን 2012 ዓ.ም ፈርመው ሰጥተውኛል፡፡ አመልካችም ክፍያ እንዲፈፅምልኝ ቼኩን ለባንኩ ቅርንጫፍ ያቀረብኩ ቢሆንም የቼክ ቁጥሩ ስለታገደ መክፈል የማይችል መሆኑን ገልጾ ነሐሴ 21 ቀን 2012 ዓ.ም ማረጋገጫ ሰጥቶኛል፡፡ ተጠሪም ክፍያውን እንዲፈጽምልኝ በተደጋጋሚ ብጠይቀውም ፍቃደኛ ስላልሆነ ብር 500,000፣ በሕጉ የተደነገገውን ኮሚሲዮን፤ ህጋዊ ወለድ እንዲሁም ወጪ እና ኪሳራ እንዲከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡ መልካም ንባብ………. Print 12037 Documents to download 214002(.pdf, 885.79 KB) - 1272 download(s)