/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

አቶ ብርሃኑ ታደሰ እና የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ቤቶች አስተዳደር ፅ-ቤት የሠ-መ-ቁጥር 190440

ጉዳዩ የመንግስት(የቀበሌ) ቤት የመከራየት መብት የሚተላለፍበትን አግባብ በተመለከተ የተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ተብሎ የቀረበ አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡ ክርክሩ በተጀመረበት በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች በተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ በወ/ሮ ሀረገወይን በላይነህ የማነህ ተከራይተዉ በያዙት በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በቤት ቁጥር 222 በሆነው ቤት ዉስጥ ከ1975 ዓ/ም ጀምሮ የስድስት ዓመት ህፃን እያለሁ ጀምሮ  እንደልጅ እያስተማሩኝ ያሳደጉኝ እና እስከአሁን ድረስ በቤት ውስጥ በመኖር ላይ እገኛለሁ፡፡ ነገር ግን አሳዳጊዬ የነበረችው ወ/ሮ ሀረገወይን በላይነህ በ1989 ዓ/ም አብረን ከምንኖርበት ቤት እኔ በማላውቀው ምክንያት ከቤት ከወጣች በኋላ አግኝቻት የማላውቅ መሆኔን በመግለፅ የመጥፋት ውሳኔ እንዲሰጠኝ ለአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አቤቱታ አቅርቤ ጉዳዩ እየታየ ይገኛል፡፡ የቤቱን ኪራይ በእሷ ስም እየከፈልኩ የምገኝ በመሆኑ በመመሪያ ቁጥር 4/2009 አንቀፅ 15/1 መሰረት የቤቱን ኪራይ ዉል በስሜ እንዲያዋውለኝ ባመለክትም ተጠሪ ሊያስተናግደኝ ፍቃደኛ አልሆነም፡፡ ስለሆነም ተጠሪ የኪራይ ውል እንዲያዋውለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡……… 

Previous Article እነ አቶ ሳሙኤል ገዛኸኝ፣ አቶ መኩሪያ ታረቀኝ እና አቶ ፍሰሃ እርቅይሁን የሰ-መ-ቁ-191141
Next Article እነ ወ-ሮ መሰረት ገብሬ እና ወ-ሮ ወርቋሃ ገብሬ የሰ-መ-ቁ 182459
Print
15595