/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

አቶ ተስፋዬ ኪዳኔ እና አቶ ወርቁ ዋበሎ የሰ/መ/ቁጥር 198071

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ የከተማ ቦታን የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች አከራካሪውን ይዞታ በመልቀቅ ለተጠሪ ሊያስረክብ ይገባል በማለት የሰጠው ውሳኔ በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች መፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አመልካች ስላመለከቱ ነው፡፡አመልካች በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት ተከሳሽ የነበሩ ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ ነበሩ፡፡

ተጠሪ የካቲት 19 ቀን 2011 ዓ.ም ጽፈው በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስም አዋሳኙ በክሱ ውስጥ የተጠቀሰውን በቢቾ ቀበሌ የሚገኘውን ይዞታ ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በስጦታ አግኝቼ ቆርቆሮ ቤት ሰርቼ የምጠቀምበትን በ2008 ዓም በተደረገው ህገ ወጥ ይዞታን ስርአት የማስያዝ አሰራር ይዤ ካለሁበት 6 ሜትር መንገድ በመውሰዱ ወደ አመልካች ይዞታ ውስጥ ሲያስገባኝ አመልካችም ከኋላ ለኔ ለቅቆ ወደፊት እንዲሸጋሸግ ሲደረግ ለኔ በተሰጠኝ ይዞታ ላይ ቤት ገንብቶ ለመልቀቅ ፈቃደኛ ስላልሆነ በራሱ ወጪ አፍርሶ እንዲለቅልኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡………….

Previous Article አቶ ዮሀንስ ክፍሉ እና አቶ ሀሰን መሀመድ የሰ/መ/ቁጥር 197942
Next Article መሀመድ አባ ቡልጉ እና የጌምቤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የሰ.መ.ቁ 198400
Print
13087

Documents to download

  • 198071(.pdf, 834.42 KB) - 1115 download(s)