Tuesday, May 20, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ ታከለ በረዳ እና እነ ብሄራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ/በቁጥር 4/ ሰ/መ/ቁ 253732 ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም አመልካች የስር የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ውሳኔ ላይ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ እንዲታረም በማለት ሲሆን የቀረበው የሰበር አቤቱታውም የኮድ- 3-93835 ኢቲእና የኮድ 3-29007 ኢቲ ተሽከርካሪዎች በሚመለከት ክፍያ ከተከፈለበት 25/06/2011 ዓ/ም ጀምሮ ሁለት አመታት ጊዜ ውስጥ 1ኛ ተጠሪ በመዳረግ መብቱ ሳይጠቀም የቆየ ስለመሆኑ በስር ፍ/ቤት የተረጋገጠ ሆኖሳለ 1ኛ ተጠሪ በእነዚህ ተሽከርካሪዎች ላይ ያቀረበው ክስ በይርጋ የሚዘጋ ሆኖ እያለ 1ኛ ተጠሪ ለተለያዩ ደንበኞች የከፈለውን የተለያየ ካሳ በሚመለከት በተለያዩ ደንበኞች እግር ተተክቶ መብቱን የሚጠይቅ እንደመሆኑ መጠን ይርጋ ያላላፈን የሌሎች ደንበኞቹን ጉዳይ አጣምሮ ስለከሰሰ ብቻ በተጠቀሱት መኪኖች ላይ የቀረበው ክስ በይርጋ አልታገደም ሊባል አይችልም፡፡የመጨረሻ ጊዜ ክፍያ የሚያገለግለው መጨረሻ ለተከፈለለት ደንበኛ ብቻ እንጂ የይርጋ ጊዜ ላለፈበት ደንበኛ ለተከፈለ ክፍያ አይደለም ስለሆነም በተጠቃሾቹ መኪኖች ላይ ክፍያ ከተፈጸመ ጀምሮ ይርጋ ያለፈበት ክስ ስለመሆኑ በስር ፍ/ቤት ተረጋግጦ እያለ የስር የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ለተለያዩ ደንበኞች እና መኪኖች የተከፈለ ካሳን መሰረት አድረጎ የቀረበን ክስ አግባብነት የሌለውን የሰ.መ.ቁ 194880 በመጥቀስ የሰጠው ውሳኔ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ እንዲታረምልን የሚል ነው፡፡ መልካም ንባብ …. Print 364 Documents to download 253732(.pdf, 851.42 KB) - 51 download(s)