/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

አቶ ታደሰ ንጉሴ እና አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ሻሸመኔ ቅርንጫፍ የሠ/መ/ቁጥር 201974

ጉዳዩ የሥራ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን አመልካች በኦሮሚያ ክልል በሻሸመኔ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ ከተጠሪ ጋር በ1989 ዓ/ም በፈፀሙት የስራ ውል በባላንስ ሠራተኛነት የስራ መደብ ላይ በወር 13,034.00 እየተከፈላቸዉ እንዲሰሩ ተቀጥረዉ ሲሰሩ መቆየታቸዉን፤ነገር ግን ያለምንም ምክንያት በቀን 07/09/2011ዓ/ም በተጻፈ ደብዳቤ የትራንዛክሽን ሥራ በመስራት በማሳለፍ ብድር በመዝጋት ባንኩ ማግኘት ያለበትን በማሳጣት ጥፋት ፈጽመሀል በማለት ሥራዬ ትራንዛክሽን ማሳለፍ ባለመሆኑ የሰራሁት ጥፋት ሳይኖር ከሕግ-ዉጭ ከሥራ አሰናብቶኛል፡፡ስለሆነም ወደ ሥራ እንዲመልሰኝ እንዲወሰንልኝ፡፡ይህ የሚታለፍ ከሆነ የስንብት ክፍያ ብር 95,582.67 ፣የ15 ቀን ደመወዝ ብር 6,517.00 ፣ክፍያ ለዘገየበት የሶስት ወር ደመወዝ ብር 39,102.00 ፣ካሳ የ6 ወር ደመወዝ ብር 78,204.00፣የፕሮቪደንት ፈንድ ክፍያ ብር 63,550.29፣ተጠሪ ባንክ በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት ከ20 ዓመት በላይ ላገለገለ ሰራተኛ 21 ካራት ወርቅ ስለሚሰጥ የዚህ ዋጋ የአንድ ካራት ዋጋ ብር 1,700.00 ብር 35,700.00፣የቦነስ ክፍያ የ2011 ዓ/ም ብር 39,102.00፣ከ2009-2011ዓ/ም ድረስ ያልተጠቀምኩበትን የሶስት ዓመት  የአመት እረፍት ወደገንዘብ ቀይሮ እንዲከፍለኝ በአቃላይ ብር 370,991.29 (ሶስት መቶ ሰባ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና አንድ ብር ከሃያ ዘጠኝ ሳንቲም) እንዲከፈላቸዉ እንዲወሰንላቸዉ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡…………….

 

 

Previous Article አቶ ሆርዶፋ ዴቲ እና ወ/ሮ ፀሐይ ሽፈራው የሰ/መ/ቁ፡-201929
Next Article ማክሼቭ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና ወጋገን ባንክ አክሲዮን ማህበር የሰ/መ/ቁ፡-201990
Print
14892

Documents to download

  • 201974(.pdf, 756.55 KB) - 1144 download(s)