/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

አቶ ኃይለጊዮርጊስ ይልማ እና አቶ አዲስ እሸቱ የሰ/መ/ቁጥር 197009

ይህ የሰበር አቤቱታ ሊቀርብ የቻለው አመልካች እና በስር ፍርድ ቤት ከ1ኛ እስከ 3ኛ የተመለከቱት ተከሳሾች አከራካሪውን ቤት ለተጠሪ ሊያስረክቡ ይገባል በማለት የስር የጣርማ በር ወረዳ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች መፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አመልካች ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ መነሻ በማድረግ ሲሆን ተጠሪ በጣርማ በር ወረዳ ፍርድ ቤት ከሳሽ የነበሩ ሲሆን አመልካች 1ኛተከሳሽ ነበሩ፡፡

ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በአመልካች እና በስር ፍርድ ቤት ከ1ኛ እስከ 3ኛ በተመለከቱት ተከሳሾች ላይ ባቀረቡት ክስም አዋሳኙ በክሱ ላይ የተመለከተውን 400 ካሜ ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤት ከነሰርቪሱ የካቲት 27 ቀን 2011 ዓም በተደረገ የሽያጭ ውል ከ1ኛ እስከ 3ኛ ከተመለከቱት ተከሳሾች በብር 200,000.00 ገዝቼ ካርታ በስሜ የተሰጠኝ ቢሆንም ቤቱን ከአመልካች ነፃ በማድረግ ያላስረከቡኝ በመሆኑ ፤አመልካችም በአደራ ይዤ የምጠቀመው ነው በማለት ምንም መብት ሳይኖረው ለማስረከብ ፍቃደኛ ስላልሆነ ከ1ኛ እስከ 3ኛ የተመለከቱት ተከሳሾች ቤትና ይዞታውን ከ3ኛ ወገን ነፃ አድርገው እንዲያስረክቡኝ አመልካችም የፈጠረውን ሁከት አቁሞ ቤትና ቦታውን እንዲያስረክበኝ ይወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል፡፡……..

Previous Article አቶ ሀብታሙ ዝናቡ እና አቶ ታሪኩ አየለ የሰ/መ/ቁ 196871
Next Article የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤሕግ እና መልካሙ ዳታ ደሴ የሰ.መ.ቁ 197432
Print
13618

Documents to download

  • 197009(.pdf, 826.1 KB) - 1242 download(s)