Friday, July 15, 2022 / Categories: CASSATION, 2013, Cassation አቶ ኃይለ ስላሴ ዮሐንስ (ሸካ ኖርዲክ ማርና ሰም ልማት) እና አልፋ ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ 1 የጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ማህበር የሰ/መ/ቁጥር 207336 አመልካች ሚያዝያ 17 ቀን 2008 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው ክስ ከተጠሪ ጋር ህዳር 25 ቀን 2008 ዓ.ም በተደረገ የጭነት ማጓጓዝ ውል ለአውሮፓ ኤክስፖርት የተዘጋጀ 20.88 ሜትሪክ ቶን ማር ወደ ጅቡቲ ወደብ ለማጓጓዝ ተስማምቶ ንብረትነቱ የስር 2ኛ ተከሳሽ የሰሌዳ ቁጥሩ 37607-07420 የሆነን ተሽከርካሪ በመመደብ ሲያጓጉዝ አሽከርካሪው በፍጥነት በማሽከርከሩ በደረሰ አደጋ ወደብ ላይ ሳይደርስ በጅቡቲ ክልል አባይ በሚባል ቦታ መኪናው ወድቆ ማሩ ፈሶ በመበላሸቱ ለውጪ ገበያ እንዲቀርብ ሳይደረግ ቀርቷል፡፡ ተጠሪ የማሩን ዋጋ ከግምት ውስጥ ሳያስገባ በገባው የጉዞ መድን ውል አመልካች ከደረሰው ጉዳት ጋር የማይመጣጠን ብር 524,843.71 ብቻ ተቀብሏል፡፡ አመልካች ከማሩ ማግኘት ይገባው የነበረው ገንዘብ፣ ማሩን ለማስመርመር ለኤስዲኤስ የተከፈለ ገንዘብ፣ የምርቱን ናሙና ለመላክ፣ ለማስመርመር እና ለመጋዘን ኪራይ የተከፈለ ገንዘብ ብር 1,975,635.52 ሲሆን በተጠሪ ትዕዛዝ ናይል ኢንሹራንስ የከፈለው ገንዘብ ተቀናሽ ተደርጎ የሚቀረውን ብር 1,449,694.90 አደጋው ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር እንዲሁም አደጋው ከደረሰበት ቀን ናይል ኢንሹራንስ ብር 524,843.71 እስከከፈለበት መጋቢት 23 ቀን 2008 ዓ.ም ድረስ ያለውን ወለድ ተከሳሾች በአንድነት እና በነጠላ እንዲከፍሉ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነተ ጠይቋል፡፡ መልካም ንባብ……. Print 12706 Documents to download 207336(.pdf, 860.53 KB) - 1018 download(s)