/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ ኒአምን ጣሂር ሀሰን እና አቶ ፈርሀን መሀመድ ሰ/መ/ቁጥር፡- 246211

ጉዳዩ የማይንቀሳቀስ ንብረትን ለመረከብ የቀረበ ክርክር ሲሆን የአመልካች የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ሆነው እያለ የሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የመዳኘት ስልጣን ሳይኖረው መወሰኑ እንዲሁም በየደረጃው ያሉት ፍርድ ቤቶችም ይህንኑ ውሳኔ ማጽናታቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በሚል የቀረበ የሰበር አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡ተጠሪ ከሳሽ ሆነው በአሁኑ አመልካች ላይ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ፍ/ቤት የመሰረቱት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- ንብረትነቱ የእኔና የወንድሜ የሆነውን በጅግጅጋ ከተማ ቀበሌ 06 የሚገኝ አራት ክፍል ቤቶች ያሉት 500ካ.ሜ ይዞታ የአሁኑ አመልካች የምንፈራቸውን ወታደሮች በመላክ ለቃችሁ ካልወጣችሁ እንገላችኋለን በማለት በመዛት እና በመሳሪያ በማስፈራራት ተጠሪ ወደ ውጭ ሀገር እንድሄድ ካደረጉ በኃላ አመልካች ለስምንት አመት ይህንኑ ቤትና ይዞታዬ በማከራየት ኪራይ የሰበሰቡ በመሆኑ በኪራይ የሰበሰቡትን 912000(ዘጠኝ መቶ አስራ ሁለት ሺህ ብር) እንዲከፍሉኝ እንዲሁም ቤትና ይዞታውን እንዲያስረክቡኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ጉዳዩ የማይንቀሳቀስ ንብረትን ለመረከብ የቀረበ ክርክር ሲሆን የአመልካች የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ሆነው እያለ የሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የመዳኘት ስልጣን ሳይኖረው መወሰኑ እንዲሁም በየደረጃው ያሉት ፍርድ ቤቶችም ይህንኑ ውሳኔ ማጽናታቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በሚል የቀረበ የሰበር አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡ መልካም ንባብ……

Print
1652

Documents to download

  • 246211(.pdf, 838.13 KB) - 220 download(s)