Friday, May 23, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation አቶ ናሁሰናይ አጥናፉ እና ኢትዮቴሌኮም ማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን የሰመ.ቁጥር 261424 ጉዳዩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የደብረ ብርሃን ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በፍሬ ጉዳዩ ላይየግራቀኙን ክስ እና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ ለዲሲፒሊን ዉሳኔዉ ምክንያት የሆነዉ ስህተት የተፈፀመዉ አመልካች በሌለበት በዝውውር ሳይመጣ የተሰራ ስራ በመሆኑ፤ ውል ተደርጎ ስራው እየተሰራ በመሆኑ አመልካች በደረሰበት ሊያስተካክለው የሚችል አይደለም ፤ አመልካች በሌለበት ለተሰራ ስራ በዲሲፒሊን መጠየቁ ተገቢ ባለመሆኑ የዲሲፒሊን ውሳኔው ሊሰረዝ ይገባልበማለት ዉሳኔ ሰጥቷል፡፡ ተጠሪ በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝቶ ይግባኝ ለሰሜን ሽዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱ በቀረበዉ ይግባኝ አቤቱታ ላይ ግራቀኝን አከራሮ የስራ ዝርዝሩ የተሰራዉአመልካች በሌለበት ግዜ ቢሆንም አመልካች ስለ ስራዉ ተጫራቾች ባቀረቡት ሰነድ የፋይናንሻል ምዘና በሚደረግበት ወቅት፣ከጨረታ አሻናፊዉ ጋር ዉል ሲፈርም፣ እና ለተቋራጩ ሳይት ሲያስረክብ ስለተፈጠረዉ ስህተት ማወቅ የነበረበት እና ስለ ስህተቱም የሚያዉቅ መሆኑን በኢሜል የገለፀ በመሆኑ ተጠሪ ለደረሰበት ጉዳት አመልካች ላይ የወሰደዉ የዲሲፒሊን ቅጣት ተገቢ ነዉ፤ ተጠሪ በአመልካች ላይ ያሳለፈው የዲስፕሊን ቅጣት ውሳኔ ሊነሳ አይገባም በማለት የወረዳውን ፍርድ ቤት ያሳለፈውን ዉሳኔ ሽሯል፡፡መልካም ንባብ …. Print 2761 Documents to download 261424(.pdf, 834.08 KB) - 311 download(s)