/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ አለማየሁ ኃ/ጊዮርጊስ እና የፍትህ ሚኒስቴር ዐቃቤ ሕግ የሰ/መ/ቁ 273144

ጉዳዩ አመልካች ሚስት የሆኑት ወ/ሮ ዓለምፀሐይ ስላሱ የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 539/1(ሀ) ተላልፈው መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም የግዲያ ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ክስ በመሠረተበት ጉዳይ የቤት ሠራተኛው የሆነችውን ግለሰብ ቅጣቱ በአንቺ ስለማይከብድ የሟች ገዳይ እኔ ነኝ በይ በማለት በተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች በመደለል እና የካሜራውን ዱካ በማጥፋት የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 445 ተላልፈዋል በሚል በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ክስ ቀርቦባቸው አመልካች ተላልፈዋል የተባሉት ድንጋጌ በቀላል እስራት ወይም በመቀጮ ስለሚያስቀጣ ዋስትናን የሚያስከልክል አለመሆኑን ጠቅሰው አስተዳደሪ እና የሕጻነት ልጆች አባት ስለሆኑ የዋስትና መብት እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል፡፡ ዓቃቤ ሕግም በቀረበው የዋስትና ጥያቄ ላይ በሰጡት መልስ አመልካች የተከሰሱበት የሕግ አንቀጽ ዋስትና የሚያስከለክል ባይሆንም በግዲያ ወንጀል የተከሰሱት ባለቤታቸው በሕግ ተጠያቁ እንዳይሆኑ ማስረጃ ለማጥፋት የሞከሩ በመሆኑ በዋስትና ቢወጡ 1ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክርንና ሌሎችንም ስለሚያባብሉ የዓቃቤ ሕግ ማስረጃ እስክሰማ ድረስ የዋስትና ጥያቄው ውድቅ እንዲሆን ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ ….

 

Print
2356

Documents to download

  • 273144(.pdf, 852.93 KB) - 334 download(s)