/ Categories: CASSATION, Cassation

አቶ አምሳሉ ቶሮ እና የብርብር ከተማ አንድነት ንግድ ማሕበር የሰ/መ/ቁ፡-209647

ጉዳዩ የከተማን ይዞታ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በደቡብ ብሔሮች ብሔረሠቦች እና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ዐባያ ወረዳ ፍ/ቤት ነው፡፡ በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን ተጠሪ ከሳሽ፤ የአሁን አመልካች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን ተጠሪ በሥር ፍ/ቤት ያቀረበው ክስ ይዘት በአጭሩ፡- አዋሳኙ በክሱ የተገለጸ እና በምዕራብ ዓባያ ወረዳ ብርብር ከተማ ቀጠና 1 ውስጥ የሚገኝ አጠቃላይ ስፋቱ 1234 ካ.ሜ የሆነ የድርጅት ይዞታ ያለው መሆኑን፤ አመልካቹ በጥቅምት ወር 2011 ዓ.ም 9.6 x 1.1 = 10.56 ካ.ሜ ድንበር አልፎ የያዘበት መሆኑን፤ አመልካች አላግባብ የያዘውን ይዞታ እንዲለቅ በተደጋጋሚ ተጠይቆ ፈቃደኛ አለመሆኑን በመግለጽ አልፎ የያዘውን ይዞታ እንዲለቅ እና ወጪ ኪሳራ የማቅረብ መብቱ እንዲጠበቅ ይወሰንለት ዘንድ ዳኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው፡፡………

Print
11908

Documents to download

  • 209647(.pdf, 934.86 KB) - 769 download(s)